Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ኢኮኖሚያዊ ትብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

0 641

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ኢኮኖሚያዊ ትብራቸውን ለማጠናከር መስማማታቸው ተገለጸ።በኢፌድሪ የንግድ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አያና ዘውዴ የተመራ የልዑካን ቡድን በዱባይ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢኮኖሚያዊ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሻዊ የንግድ እና የኢንቨትመንት ጉዳዮች ላይ መክሯል።በዚህም የዱባይ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ያሉትን ምቹ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የቱሪዝም እና የንግድ ኢንቨስትመንት አማራጮች ተጠቅመው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ቀርቧል።የንግድ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አያና ዘውዴ ሁለቱ ሀገራት በስጋ እና በእንስሳት ሀብት ያለው የንግድ ትብብራቸው ስኬታማ እንዲሆን ለማድረግ በጋራ መስራት እንዳለባቸው ነው የጠቆሙት።የተባበሩትዓረብ ኤምሬቶች በኢትዮጵያ የግብርና፣ የምግብ እና የመድሃኒት ኢንዱስትሪዎች በመሰማራት ያገኘቻቸው መልካም ልምዶች በሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮች እንድትሰማራ እንደሚያደርጓትም ተነግሯል።ሀገሪቱ በሲቪል አቪየሽን፣ በግብርና በመሰረተ ልማት እና በቱሪዝም ዘርፎች በኢትዮጵያ መሰማራት እንደምትፈልግም በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የውጭ ንግድ እና የኢንዱስትሪዎች ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ዋና ፀሃፊ አብዱላህ አል ሳሌህ ተናግረዋል። ምንጭ፡- Emirates News Agency

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy