ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ኢኮኖሚያዊ ትብራቸውን ለማጠናከር መስማማታቸው ተገለጸ።በኢፌድሪ የንግድ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አያና ዘውዴ የተመራ የልዑካን ቡድን በዱባይ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢኮኖሚያዊ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሻዊ የንግድ እና የኢንቨትመንት ጉዳዮች ላይ መክሯል።በዚህም የዱባይ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ያሉትን ምቹ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የቱሪዝም እና የንግድ ኢንቨስትመንት አማራጮች ተጠቅመው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ቀርቧል።የንግድ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አያና ዘውዴ ሁለቱ ሀገራት በስጋ እና በእንስሳት ሀብት ያለው የንግድ ትብብራቸው ስኬታማ እንዲሆን ለማድረግ በጋራ መስራት እንዳለባቸው ነው የጠቆሙት።የተባበሩትዓረብ ኤምሬቶች በኢትዮጵያ የግብርና፣ የምግብ እና የመድሃኒት ኢንዱስትሪዎች በመሰማራት ያገኘቻቸው መልካም ልምዶች በሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮች እንድትሰማራ እንደሚያደርጓትም ተነግሯል።ሀገሪቱ በሲቪል አቪየሽን፣ በግብርና በመሰረተ ልማት እና በቱሪዝም ዘርፎች በኢትዮጵያ መሰማራት እንደምትፈልግም በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የውጭ ንግድ እና የኢንዱስትሪዎች ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ዋና ፀሃፊ አብዱላህ አል ሳሌህ ተናግረዋል። ምንጭ፡- Emirates News Agency