NEWS

ኢትዮጵያን የአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለማድረግ እየሰራ መሆኑ መንግስት ተገለጸ

By Admin

March 13, 2017

ኢትዮጵያን የአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለማድረግ የተቀመጠውን ራዕይ እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪያል ፓርክ ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡የኮርፕሬሽኑ ሊቀመንበር ዶ/ር አርከበ እቁባይ እንደገለጹት አገሪቱን የአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለማድረግ የኢነርጂና የትራንስፖርት ዘርፎች ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፡፡

እ.አ.አ ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ የሀገሪቱ ምጣኔ ሃብት ፍጥነት እያደገ በመምጣቱ ባለፉት 13 አመታት ውስጥ ጠቅላላ አገራዊ ምርቱ በ11 በመቶ እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በዚህም ሀገሪቱ ከግብርና ወደ ኢንደስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር እየሰራች መሆኗን ገልጸዋል፡፡

መንግስትም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ፤ የሀገሪቱን ምጣኔ ማሳደግ፤ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ወጣቶች የስራ እድልን መፍጠርና የወጪ ንግድ መጠንን ማሳደግ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ነው የገለጹት፡፡የኢንደስትሪ ፓርኮቹ ለሀገሪቱ 100 ቢሊዮን ዶላር ያህል ገቢ ያስገኛሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ምንጭ፡- ብሉምበርግ