CURRENT

ኢትዮጵያ ለምን ትጎበኛለች?

By Admin

March 11, 2017

ኢትዮጵያ ለምን ትጎበኛለች? The wiki has landed

በየአገራቱ እየጎበኘ ለአውሮፓ ጎብኝዎች ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻዎችን የሚጠቀመው “The wiki has landed” ድረ ገጽ ጋዜጠኛ ኢያን ሼልስ በቅርቡ ኢትዮጵያን ጎብኝቶ ነበር፡፡ ኢያን ሼልስ ምዕራባዉያን ሚድያዎች ስለ ኢትዮጵያ የሚዘግባቸው አብዛኛዎቹ ዘገባዎች ሀሰት ነገር ሀሰት መሆኑን ይናገራል፡፡ በተቃራኒው የአውሮፓ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን መጎብኘት ያለባቸውን 14 ምክንያቶች ከነፎቷቸው ጭምር በማስደግፍ ያስረዳል፡፡1. ኢትዮዽያ ለም አገር በመሆኗ 2.ረሃብ የሌለባት ምግብ የሞላባት አገር በመሆኗ 3.ህዝቦቿ ሰላምተኞችና ታማኞች በመሆናቸው 4.ሁሉም ነገር ለምለምና ማራኪ በመሆኑ ኦርጅናል ቀለሞችን ስለምናገኝ 5.የራሷባህልና ታሪክ ያላት እንዲሁም የስልጣኔ ምንጭ መሆኗ 6.ብርቅየ የዱር እንስሳት ስለሚገኙባት 7.ህዝቦቿ ትጉህ ሰራተኞችና በስራ ተጠምደው የሚዉሉ መሆናቸው 8.የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በቀላሉ የሚገኝባት አገር መሆኗ 9.በአገሪቱ የሚመረቱ የቢራ መጠጦች ጣእማቸው ልዩ መሆኑ 10.የተለያዩ አመለካከቶች የሚንጸበራቁባት በመሆኑ ህዝቦቿ አይሰለቹም 11.ሁሉም አካባቢዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆናቸው 12. ህዝቦቿም ደን የማያወድሙ መሆናቸውን ተከትሎ አገሪቱ በተለያዩ የእፅዋት አይነቶች የተሸፈነች መሆኗ 13.የቡናው ጣእም የተለየ መሆኑ 14.በኢትዮዽያ የሚታየው ነገር ሁሉ ማራኪ፡ አስደሳችና ቀልብ ሳቢ በመሆኑ አገሪቱን ለመጎብኘት ጉጉት የሚያሳድሩ በመሆናቸው ሊጎበኙ ይባል ይላል የ”The wiki has landed” ድረ ገጽ ጋዜጠኛ ኢያን ሼልስ፡፡ምንጭ፤ The wiki has landed