Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር እያደረገች ያለውን ጥረት እንግሊዝ እንደምትደግፍ ገለጸች

0 865

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በቀጣናና በአህጉር ደረጃ ሰላም ለማስከበር የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ እንግሊዝ ገለጸች።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱ ወቅት ሁለቱ አገሮች የጋራ አቋም በሚይዙባቸው አለም አቀፍ ጉዳዮች፣ በልማት፣ በጸጥታ፣ በኢኮኖሚ ትብብር፣ በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ አብሮ ለመስራት መስማማታቸው ነው የተገለጸው።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላምና መረጋጋትን ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት የእንግሊዙ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድንቀዋል። ለአፍሪካና ሌሎች የዓለም አገሮች ወሳኝ ሚና እየተጫወተችም መሆኑን ነው የተናገሩት።ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበርና ሌሎች ዘርፎች ትልቅ አቅም እንዳላት ነው የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆንሰን የገለጹት።

አገሪቷ እንደ ጎረቤት አገርና ኢጋድ መሪነቷ የሶማሊያ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ያደረገችው ጥረት እንግሊዝ እንደምታደንቅ በመግለጽ በጋራ ለመስራት አገራቸው ዝግጁ መሆኗን አብራርተዋል።አገራቱ በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ አብረው ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያም መወያየታቸው ነው የተገለጸው።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን አየር መንገድ የጎበኙ ሲሆን፤ “በአየር መንገዱ ያየሁት ነገር የኢትዮጵያን ትልቅ ስኬት የሚያሳይ ነው” ብለዋል።ውይይቱን የተከታተሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ እንደገለጹት፤ ሁለቱ ሚኒስትሮች ያደረጉት ምክክር የአገሮቹን ግንኙነት ለማስፋት መንገድ የቀየሰ ነው።

የእንግሊዝ ባለሃብቶች በቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ በቢራ ምርትና ሌሎች ዘርፎች መሰማራታቸውን ያስታወሱት ቃል አቀባዩ፤ በትምህርት ዘርፍም እንዲሳተፉ ዶክተር ወርቅነህ መጠየቃቸውን ነው የገለጹት።

የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ስትራቴጂያዊና በአርአያነት ሊጠቀስ እንደሚችል ይነገራል። አገሮቹ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን እኤአ በ1897 መጀመራቸው ይታወቃል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy