Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምትገነባቸው ፕሮጀክቶች ዓለም አቀፍ የውሃ ህግጋትን የተከተሉ ናቸው- ምሁራን

0 659

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ ታላቁን የህዳሴ ግድብ ጨምሮ በአባይ ወንዝ ላይ የምትገነባቸው ታላላቅ ፕሮጀክቶች ዓለም አቀፍ የውሃ ህግጋትን መሰረት ያደረጉ መሆናቸውን የዘርፉ ምሁራን ገለጹ።

የአገሪቱ ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም የላይኛውና ታችኛው ተፋሰስ አገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።

በተፋሰሱ አገራት መካከል ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም እንዲኖር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1999 “የናይል የትብብር መድረክ” መቋቋሙ ይታወቃል።

በትብብር መድረኩ ከተሳተፉ ዘጠኝ አገራት ሱዳንና ግብጽ ስምምነቱን ሳይቀበሉ የቀሩ ሲሆን ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ስምምነቱን ተቀብላ ነገር ግን አልፈረመችም።

ስምምነቱን ያልተቀበሉና ያልፈረሙ አገራት በቅኝ ግዛት ወቅት የወጣውን ኢ-ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም ለመተግበር በማሰብ እንጂ የኢትዮጵያ የውሃ አጠቃቀም የተፋሰሱን አገራት ጥቅም የሚነካ ሆኖ አይደለም።

የምስራቅ ናይል ቴክኒካል አህጉራዊ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ የምትገነባቸው ታላላቅ ፕሮጀክቶች የዓለም አቀፉን የውሃ ህግ የተከተሉ ናቸው።

“የኢትጵያ የውሃ ኃብት አስተዳደር ፖሊሲ የወሰን ተሻጋሪ ውሃን በተለመከተ ያስቀመጣቸው መርሆች አሉ። እነዚህ መርሆች በፍትሃዊና ምክንያታዊ አጠቃቀም ላይ የተመሰረቱ በሀገራት መካከል ቅርብ ግንኙነት እንዲፈጠርና ቀጠናዊ ትስስር እንዲኖር የሚያመቻች ፖሊሲ ነው።  

የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን አስተዳደር መርሆ መሰረት ያደረገ ነው።

ኢትዮጵያ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ባለፈ የጣና በለስን፣ የቆቃ የኃይል ማመንጫና ሌሎችን የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ስትገነባ የወንዙን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት መርህ መሰረት ያደረገ እንደነበር ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህርና በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ጥናት ያደረጉት ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ የኢትዮጵያ የአባይ ወንዝ የውሃ አጠቃቀም ዓለም አቀፉን የውሃ ህግ የተከተለና የተፋሰሱን አገራት ጥቅም የማይጎዳ ነው ብለዋል።

“ኢትዮጵያ የውሃ ሃብቷን ስትጠቀም የውሃ አመንጪ እንደመሆኗ እንደማንኛውም ውሃ አመንጪ አገር ውሃ ፈሶ የሚሄድባቸው አገር ህዝቦችንም ሆነ የመንግስታቱን ልማት በማይጎዳ መንገድ በጥንቃቄ የመጠቀም ሁኔታ ነው የሚጠበቀው። ኢትዮጵያም እያደረገች ያለችው ይሄንን ነው፤ ኢትዮጵያ ድንበር ተሻግረው የሚሄዱ ብዙ ወንዞች አሏት፤ እነዚህን ወንዞች ስራ ላይ በማዋል የአገሪቱን ልማት ከፍ ለማድረግ መጠቀሙን ትቀጥላለች። ስትጠቀም ጎረቤቶቿን ለመጉዳት ሳይሆን እነሱ በማይጎዱበት ሁኔታ ይልቁንም ከእነሱ ጋር በመተባበር ከኢትዮጵያ ጋር ጥቅሙን የሚጋሩበት ሁኔታ እየፈጠረች ይሄንን እያግባባች ነው እየሰራች ያለችው።”

ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝን ውሃ የምትጠቀምበት ስርዓት የተፋሰሱን አገራት ፍትሃዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የጋራ ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑን አስረድተዋል ዶክተር ያዕቆብ።

የትብብር ስምምነቱን ያልፈረሙና ያልተቀበሉ አገራትም ተቀብለው ከመፈረምና በጋራ ከመስራት ውጭ ሌላ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አማራጭ እንደሌላቸው ነው ያስረዱት።

ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ያላት ድርሻ 86 በመቶ ቢሆንም ለመስኖ ልማት የምትጠቀምበት የውሃ መጠን ከ 0 ነጥብ 2 ቢሊዬን ኪዩቢክ ሜትር አይበልጥም ነበር፤ ግብፅ ከምትጠቀምበት 40 ቢሊዬን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ጋር ሲነፃፀር በወንዙ ላይ የነበረውን ኢ-ፍትሃዊ አጠቃቀም ያሳያል

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy