Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በአባይ ውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ያደረገችው ውይይት ውጤታማ ነው -ውጭ ጉዳይ

0 559

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ የአባይ ውሃን ከተፋሰሱ አገራት ጋር በፍትሃዊነት ለመጠቀም ስታደርግ የነበረው ውይይት ውጤታማ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአውሮፓ ህብረት ልዑካን ገለጸ።ሚኒስትር ደኤታዋ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ህብረት የልዑካን ቡድን አባላት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

የቡድኑ አባላት ከአባይ ውሃ አጠቃቃም፣ በአገሪቱ ስላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ ከዜጎች ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ዙሪያ እየተጫወተች ስላለው ሚና ጥያቄዎችን አንስተዋል።

ወይዘሮ ሂሩት በሰጡት ማብራሪያ ”በአባይ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ ወንዙን በጋራ መጠቀም በሚቻልበት ዙሪያ ተከታታይ ውይይት ስታደርግ ቆይታለች” ”ውይይቱም ውጤት አምጥቷል” ያሉት ወይዘሮ ሂሩት ኢትዮጵያ የአባይ ውሃንን በፍትሃዊነት የመጠቀም አቋሟን እንደምትቀጥልበት ነው ያረጋገጡት።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ እየተጫወተች ስላለው ሚናም ለልዑካን ቡድኑ አብራርተዋል። በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን ኢትዮጵያ በኢጋድ በኩል እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኑን ጠቅሰው በአገሪቱ ሠላም እንዲሰፍን የተፈረሙ ስምምነቶች እንዲተገበሩ ግፊት ማድረጓን ትቀጥላለች ብለዋል።

የቀጣናውን ሠላም ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ ያላሰለሰ ጥረት እያደረገች መሆኗን የገለጹት ሚኒስትር ደኤታዋ በሶማሊያ አልሸባብ ለመዋጋት በአሚሶም በኩል እያደረገች ያለውን አስተዋጽኦ በማሳያነት ጠቅሰዋል።በሶማሊያ ሠላም ከማስፈን ሥራው ባለፈ የአገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲጠናከር ኢትዮጵያ የአቅም ግንባታ ድጋፍ እያደረገች መሆኑንም ተናግረዋል።

“ሆኖም ኤርትራ በሽብርተኝነት ከተፈረጁ ቡድኖች ጋር በማበር ኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ለማድረስ በተለያዩ ጊዜያት ሙከራ እያደረገች መሆኑ ፈተና ነው” ሲሉ ለልዑካን ቡድኑ አባላት አብራርተዋል።የአውሮፓ ህብረት የኤርትራ መንግሥት የሚያደርገውን ትንኮሳ እንዲያቆም የመፍትሄ እርምጃ እንዲወስድም ጠይቀዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ከአገሪቱ ኢኮኖሚና ሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ በሚቀጥሉት ዓመታት ለሁለት ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል።በሁለተኛው የእድገትና ትራንፎርሜሽን ዕቅድ ዓመታት የኢንዱስትሪ ሽግግሩን እውን ለማድረግ መንግሥት እየሰራ መሆኑን በማንሳት።

ሦስት የግብርና ማቀነባበሪያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች መገንባታቸውን ገልጸው በቀጣይም ይሄው ተግባር እንደሚቀጥል አስረድተዋል።መንግስት በተያዘው ዓመት በአገሪቱ ተከስቶ የነበረውን ግጭት ተከትሎ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዳይከሰቱ ሲሰራ መቆየቱንም አንስተዋል።የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በግጭቱ ወቅት የነበረውን የሰብአዊ መብት አያያዝ የሚያሳይ ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡንም ጠቅሰዋል።

በአገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋት በአሁኑ ወቅት የ22 ፓርቲዎች ክርክር መጀመሩንም ወይዘሮ ሂሩት ለአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን ሌላው ያብራሩት ጉዳይ ነው።

ምንጭ ፦ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy