Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ አዲስ የግብርና ኤክስቴንሽን ስትራጂ ይፋ አደረገች

0 3,577

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት  ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ የሚደረግ አዲስ የግብርና ኤክስቴንሽን ስትራቴጂ አደረገ፡፡የኤክስቴንሽን ስትራቴጂው አገሪቱ ለያዘችው  ዘመናዊ ግብርናን የመፍጠር ዓላማ ለማሳካትና  ምርትና ምርታማነትን  ለመጨመር ይረዳል ተብሏል፡፡የእርሻና ተፈጥሮ ገብት ሚኒስቴር  ከኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን  ኤጀንሲ ጋር በትብብር ጥናት አካሂዶ ነው ስትራቴጂውን ይፋ ያደረገው፡፡

ይህም በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎሜሽን  እቅድ መጨረሻ  አገሪቱ 500 ሚሊዮን ኩንታል ለማምረት የያዘችውን እቅድ  ማሳኪያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡በተለይም ኢንዱስትሪ ወደ ሚመራው  ክፍለ ኢኪኖሚ  ለመሸጋገር  በአገር ውስጥ እየተበራከቱ የመጡ ኢንዱስትሪዎችን በአገር ውስጥ ጥሬ ዕቃ ለመሸፈን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ስትራቴጂው ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

የኤክስቴንሽን ስትራቴጂው  የሴቶችና ወጣቶች  ተጠቃሚ የሚያሳድግ ፣ ሁሉንም  ማህበረሰብ  የሚያሳትፍና የአገሪቱን  የተለያየ የስነ ምህዳር ሁኔታን  ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚንስትሩ ዶ/ር እያሱ አብርሃ ተናግረዋል፡፡ምርትና ምርታማትን ለማረጋገጥ ሁነኛ ሚና ይጫወታልም ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

ስትራቴጂው  ከዚህ ቀደም የነበሩ ውስንነቶች   እንደ ገበያ ተኮር አመራረት፣ዳካማ ቅንጅታዊ አሰራር ፣የባለሙያዎችን  እውቀትና ክህሎት ለማሻሻል እንደሚረዳም ታምኖበታል፡፡በተለይም የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላትን  ለማጠናከር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

አዲሱ የኤክስቴንሽን ስትራቴጂ የግብርናው መስክ የሚፈልገውን ግንዛቤ  ለማሳደግ ፣ የአካባቢ ጥበቃን  ለማረጋገጥ፣ ግብርናውን ለማዘመንና ምርታነትን የማሳደግ  ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡

ክልሎች  እንደየነባራዊ ሁኔታቸው  ተግባር  እንደሚያውሉትም ተገልጿል፡፡ ሪፖርተር፡‑ ሙሉጌታ ተስፋዬ

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy