ኢትዮጵያ ዘላቂነት ያለው ኢንዱስትሪ መሪ ኢኮኖሚን ለመገንባት የምታደርገው ጥረት በአፍሪካ አህጉር በቀዳሚነት የአፍሪካ ተምሳሌት መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ኘሬዝዳንት ፒተር ቶምሰን ገለፁ፡፡
የጉባኤው ኘሬዝዳንት የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጐብኝተዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ኘሬዝዳንት ፒተር ቶምሰን በኢትዮጵያ እያደረጉት ያሉት የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አካል ነው በቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ፓርክ ያደረጉት ጉብኝት፡፡
ፕሬዝዳንቱ በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገኙ ፋብሪካዎችን ከጎበኙ በሃላ በሰጡት አስተያየት መንግስት አገሪቱን ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለማሸጋገር የያዘውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በጥቂት አመታት ውስጥ የኢኮኖሚ መሰረቷን ወደ አምራች ኢንዱስትሪ ለማሸጋገር እንደምትችልም ጠቁመዋል፡፡
ሪፖርተራችን አየለ ጌታቸው ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል፡፡