Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ ከአለም ባንክ የ18 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች

0 643

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአለም ባንክ በኦሮሚያ ክልል ለተመረጡ የደን ልማትና የመሬት አስተዳደር ፕሮጀክቶች የሚውል የ18 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚንስቴር በኩል አደረገ፡፡

ባንኩ ዛሬ ያደረገው ድጋፍ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ መርሃ ግብር ማስተግበሪያ በኦሮሚያ ክልል ለተመረጡ የደን ልማት ፕሮጀክቶች ከሚዉለው የ68 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አካል መሆኑም ታውቋል ፡፡

መርሀ ግብሩ  በአካባቢው ማህበረሰብ ሊከናወኑ የሚችሉ እንደ  የደን ቱሪዝም  የመሳሳሉ ከአካባቢ ጋር ተስማሚነት ያላቸውን ስራዎቸ ለማስፋፋት እንደሚውልም ተገልጿል፡፡

ከኢትዮጵያ በኩል በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚንስቴር ሚንስትር ድኤታ አቶ አድማሱ ነበበ ከአለም ባንክ የአዲስ አበባ ተወካይ ካሎሬን ቱርክ ድጋፉን ተረክበዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ሙሉጌታ ተስፋዬ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy