ኢትዮጵያ የደን ሀብቷን መጠበቅ የሚያስችላትን የ18 ሚሊየን ዶላር እርዳታ ስምምነት ከአለም ባንክ ጋር ተፈራረመች
የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል የደን ሃብትን በዘለቄታ ለማስተዳደር፣ለኢንቨስትመንት እና የበካይጋዝ ልቀትን ለመቀነስ የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መፈራረሙን አፍሪካ ቢዝነስ ኮሚኒት ድረ ገፅ ዘገበ፡፡
የ18 ሚሊየን ዶላር እርዳታው የተደረገው በአለም ባንክ ባዮ ካርበን ፈንድ(ቀጣይነት ያለው የደን መልክአ ምድርን መጠበቅ) ሲሆን መንግስት ለያዘው Oromia Forested Landscape Program (OFLP)የሚደግፍ ይሆናል ፡፡
እርዳታው ማህበረሰቡን ማዕከል ያደረጉ ስራዎች የሚከናወኑበት ሲሆን የደን ውድመትን የሚቀንሱ፣ ከመሬት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚፈጠር የበካይ ጋዝ ልቀትን እንዲሁም ከፍተኛ የደን ውድመት ይታይባቸዋል የተባሉ 49 የኦሮሚያ ወረዳዎች ላይ የደን የካርበን ይዘታቸውን የሚያሻሽሉበት ሁኔታ ይመቻቻልም ተብሏል፡፡
የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገምም የመሬት አጠቃቀም ተሞክሮው ወደ ሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች እንደሚስፋፋ ዘገባው አመልክቷል፡፡
Next Post
- Comments
- Facebook Comments
Follow Us @ethiopiaprosperous
porn videos