Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ኢንተርኔት ሲቋረጥ ያልተጠቀሙበትን ሂሳብ መጠቀም የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ አደረገ

0 474

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮ ቴሌኮም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የሞባይል ዳታ ኢንተርኔት አገልግሎት ሲቋረጥ ደንበኞች ያልተጠቀሙበትን ሂሳብ መልሰው የሚጠቀሙበትንና የአገልግሎት መጠቀሚያ ጊዜውን ማራዘም የሚያስችል ስርዓት ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል።

ደንበኞች ያልተጠቀሙበትን ቀሪ ሂሳብና የሚያበቃበትን የአገልግሎት ጊዜ ወደ *804# በመደወል ማወቅ የሚችሉበት ስርዓት መመቻቸቱን ኩባንያው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በዚህም መሰረት ለቅድመ ክፍያ፣ ለቢዝነስ ሞባይል ተጠቃሚዎች፣ ለድምጽና ዳታ ጥቅል አገልግሎት እንዲሁም ለገበታ ጥቅል እና የስጦታ አገልግሎት ደንበኞች የአገልግሎት መጠቀሚያ ጊዜን አራዝሟል።

ለሞባይል ድህረ ክፍያ ዳታ አገልግሎት የዳታ ብቻ አገልግሎት እና የጥቅል አገልግሎት ደንበኞች ያልተጠቀሙበትን ሂሳብ መልሰው በቀጣይ መጠቀም የሚችሉበት ሁኔታ ተመቻችቷል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy