Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኤጀንሲው ከዓለም የምግብ ፕሮግራም የእህል ጥራት መጠበቂያ መሳሪያዎች ድጋፍ አገኘ

0 472

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የስትራቴጂክ መጠባበቂያ ምግብ ክምችት ኤጀንሲ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም 600 ሺህ ዶላር ዋጋ ያላቸው የእህል ጥራት መጠበቂያ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገለት።

የእህል ጥራት መፈተሻ፣ ማበጠሪያና ማሸጊያ፣ መሰላል፣ ሚዛን፣ የተባይ ማጥፊያ መድሃኒት መርጫ፣ የአፍላቶክሲን መለኪያ፣ የደህንነት መጠበቂያና ሶስት ተሽከርካሪዎች ለኤጀንሲው ከተሰጡ መሳሪዎች መካከል ናቸው።

በኤጀንሲው የጥራት ቁጥጥር ስራ አመራር ዳይሬክተር አቶ አለም ወልዴ “ኤጀንሲው ከተቋቋመ ረጅም ዓመት ቢሆነውም በአቅም ውስንነት ሳቢያ ረጅም ጊዜ ያገለገሉ የጥራት መፈተሻ መሳሪያዎቹን መቀየር አልቻለም” ብለዋል።

በድጋፍ የተገኙት መሳሪያዎች ዘመናዊ በመሆናቸው ከውጭ የሚገቡና የአገር ውስጥ እህሎች ወደ መጋዘን ከመግባታቸው በፊትና ከገቡም በኋላ ጥራታቸው መጠበቁን ለማረጋገጥ ያግዛሉ።

መሳሪያዎቹ የኤጀንሲውን የእህል ክምች ጥራት አስተማማኝ ለማድረግ እንደሚያግዙም ገልጸዋል።መሳሪያዎቹ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሽንሌ፣ ኮምቦልቻ፣ ወረታና መቀሌ ለሚገኙት የኤጀንሲው መጋዘኖች ይከፋፈላሉ ተብሏል።

በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ተጠሪ ጆን አይሊፍ መሳሪያዎቹ ኤጀንሲው ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ  የሚያከማቸውን እህል ጥራት ማስጠበቅ እንደሚያስችለው ተናግረዋል።

በቀጣይም “ከኤጀንሲው ጋር በሰው ሃይል ልማትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ እንሰራለን” ብለዋል።

የኤጀንሲው ሰራተኞች ስለ መሳሪያዎቹ አጠቃቀም ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ከስዊዘርላንድና ቤልጂየም በመጡ ባለሙያዎች ስልጠና እንደሚሰጣቸው ከኤጀንሲው የተኘው መረጃ ያመለክታል።

ኤጀንሲው ብሄራዊ የስትራቴጂክ መጠባበቂያ ምግብ ክምችት አቅምን ለማሳደግ በ2010 ዓ.ም በሻሸመኔ፣ ፍኖተ-ሰላም፣ ባሌ ሮቤ፣ ነቀምት፣ ሆሳዕና፣ ነገሌ ቦረናና ቀብሪደሃር መጋዝኖች ለመገንባት አቅዷል።

አዲስ የሚገነቡት መጋዘኖች ከ892 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ እህል ማከማቸት የሚችሉ ሲሆን የነበረውን ብሄራዊ የእህል ክምችት አቅም ወደ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ያሳድጉታል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy