እዚህ ሀገር ላይ የፌደራሊዝምን ሥርዓት ከመሠረቱት ውስጥ እኛ ትልቅ ድርሻ አለን፡፡ አንዳንዴ የፌደራሊዝም ሥራዓቱ ይቅርና በሀገር ምስረታ ያለንን ድርሻ ዘንግተን የሠራናቸውን ሥራዎች የምንተውበት ጊዜ አለ፡፡ ይህቺ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንድትፈጠር ይሄ ህዝብ (ኦሮሞ) ትልቅ ድርሻ አለው፡፡ ይሄንን የፌደራል ሥረዓት በመፍጠር ረገድም ሚና አለውው፤ በፌደሬሽኑ ውስጥ የሚገባንን ለማግኘት መታገል ማለትም ይሄው ነው፡፡ሥርዓቱን መፍጠር ብቻም ሳይሆን የፈጠርነው ሥርጭት ለህዝባችን የሚጠቅም፣ የሚበጅ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ይሄንን ስንል በዚህ ፌደራሊዝም ሥርዓት ውስጥ ምንም አይነት ችግር አይገጥመንም ሁሉንም ነገር ቤታችን ውስጥ ተቀምጠን ይመጣልናል ብለን የምንጠብቅ ከሆነ ስህተት ነው፡፡ የጥቅም ግጭቶች ይኖራሉ፡፡ ይህም በፌደሬሽን ውስጥ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ለጥቅማችን ታግለን ተከራክረን የዚህን ህዝብ ጥቅም ማስጠበቅና ማስከበር አስፈላጊ ነዉ፡፡ ይሄን ማለት ሌላ ነገር መሆን ማለት አይደለም።” አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት