NEWS

ኦህዴድ የህዝቡን ጥያቄና ቅሬታ ለመመለስ በትኩረት እንደሚሰራ ገለጸ

By Admin

March 26, 2017

በ1982 ዓ.ም መጋቢት 17 የተመሰረተው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድ 27ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች ማክበር ጀምሯል፡፡በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በተገኙበት የተለያዩ የልማት ተቋማት በመመረቅ የምስረታ በዓሉን ተከብሯል፡፡ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ ኦህዴድ ህዝቡን በማሳተፍ ለህዝቡ ልማትና እድገት የሚሰራ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል፡፡