Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

“ኦባማኬር”ን የሚተካው የጤና መድህን እቅድ ይፋ ሆነ

0 977

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአሜሪካ የሪፐብሊካኖች ምክር ቤት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አሻራ ያረፈበትን የጤና መድህን ህግ (ኦባማኬር) የሚተካ አዲስ እቅድ ይፋ አድርጓል።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ፖል ሪያን ረቂቅ ህጉ፥ “ወጪ የሚቀንስ፣ ውድድርን የሚያበረታታ፣ ለሁሉም አሜሪካውያን ጥራት ያለውና አዋጭ የጤና መድህን ዋስትና ለማቅረብ ወሳኝ ነው” ብለዋል።

ረቂቅ ህጉ የጤና መድህን የማይገዙ ዜጎች ቅጣት እንዲጣልባቸው ያዛል።

አዲሱ እቅድ የጤና ጥበቃ ወጪዎችን ይጨምራል በሚል ዴሞክራቶች እየተቃወሙት ነው።

አፎርደብል ኬር አክት ወይንም በተለምዶ ኦባማ ኬር የሚሰኘው የጤና መድህን ህግ 20 ሚሊየን ከዚህ ቀደም የጤና መድህን ሽፋን ያልነበራቸውን ዜጎች ተጠቃሚ ማድረጉ ይነገራል።

ይሁን እንጂ ለጤና መድህን በየወሩ የሚከፈለው ገንዘብ እየጨመረ መምጣቱ በርካታ አሜሪካውያንን እንዳላስደሰተ ነው የሚገለፀው።

በሪፐብሊካኖች የቀረበው አዲሱ እቅድ ደግሞ ለአሜሪካውያን በዝቅተኛ ወጪ የጤና አገልግሎት ለማቅረብ የፌዴራል መንግስቱ ሚና እንዲቀንስ የሚያደርግ ነው።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኮንግረንሱ ጋር በመሆን ኦባማኬርን ውድቅ በማድረግ በአዲሱ ህግ ለመተካት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ዋይት ሀውስ ይፋ አድርጓል።

ትራምፕ በ2010 ይፋ የሆነውንና የኦባማ አሻራ እንዳረፈበት የሚነገረውን አፎርደብል ኬር አክት “አደገኛ” በማለት የገለጹት መሆኑ ይታወሳል።

አዲሱ የሪፐብሊካኖች እቅድ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የጤና መድህን ሽፋን ያልተሰጣቸውን የተወሰኑ ዜጎች እንደሚያካትት ተገልጿል።

አራት የሪፐብሊካን ሴናተሮች በኦባማኬር አስፈላጊው የጤና መድህን ሽፋን የተሰጣቸው አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በአዲሱ ረቂቅ ህግ ላይ ተገቢው ትኩረት እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል።

ትናንት ይፋ የተደረገው ረቂቅ ህግ ከኦባማኬር ይዟቸው የሚቀጥሉ ነጥቦችም አሉ።

ከእነዚህም መካከል እስከ 26 አመት እድሜ ያላቸው ሰዎች በቤተሰቦቻቸው የጤና መድህን ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችለው አንዱ ነው።

ሪፐብሊካኖች ይፋ ያደረጉት አዲስ የጤና መድህን ረቂቅ ህግ ከኦባማኬር በብዙ መንገድ የሚለይ አይደለም፤ የመድህን ዋስትና ክፍያውም በጣም ከፍተኛ በመሆኑ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች አዋጭ አይደለም የሚሉ ትችቶች እየተሰነዘሩበት ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy