NEWS

ኦካይ አፍሪካ የተሰኘ ተቋም ለኢትዮጵያዊቷ ሩታ ነጋ እውቅና ሰጠ

By Admin

March 14, 2017

በስራቸው ለተመሰገኑ ለ100 የአፍሪካ ሴቶች እውቅናን የሰጠው ኦካይ አፍሪካ ሩታ ነጋ በአፍሪካውያን ሴቶች በሰራችው ስራ ለብዙ ሴቶች ምሳሌ ልትሆን የምትችል ሴት ሲል እውቅናን ሰጥቷል፡፡ ሩታ ተዋናይ ስትሆን በ2016 ላቪንግ በተሰኘ ፊልም ላይ ባሳየችው ብቃት ለኦስካር ሽልማት ታጭታም ነበር፡፡ሌላዋ እውቅና የተሰጣት የጎረቤት ሃገር ልጅ የሆነችው ሶማሊያዊቷ ልዋድ ኢልማን ናት ይህች ሴት በሱማሊያ ጉዳይ ላይ ዋነኛ ተዋናይ በመሆን ትታወቃለች፡፡ ልዋድ ሃገሯ ሱማሊያ ከገባችበት ማህባራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ እንድትወጣ ሰፊ ጥረት እያደረገች ያለች ሴት መሆኗ ለእውቅና እንዳበቃት በእውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርአቱ ላይ ተገልጹአል፡፡ሌላዋ ተሸላሚ ሉፒታ ንዮንግ ትባላለች ኬኒያዊት ስትሆን ቲወልቭ ይርስ ሰሌቭ በተሰኘ ፊልም ላይ ባሳየችው የትወና ብቃት ለኦስካር ተመርጣ የነበረ ሲሆን በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ተሳትፎ በማድረግ ለበርካታ ሴቶች ምሳሌ መሆን በመቻሏ ለአውቅና ሽልማት አብቅቷታል፡፡ ምኝጭ፡-ሲኤን ኤን