NEWS

ከህዳሴው ግድብ ሩጫ ተሳታፊዎች 21.7 ሚሊዮን ብር ተገኘ

By Admin

March 08, 2017

ባለፈው እሁድ በመላው አገሪቱ በተካሄደው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ሩጫ 21 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ከቲሸርት ሽያጭ መገኘቱን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የቀረበው ቲሸርት ከተሳታፊዎች ያነሰ በመሆኑ አብዛኞቹ ያለቲሸርት መሳተፋቸውን ጽህፈት ቤቱ ገልጿል፡፡

በውድድሩ አዲስ አበባ 77 ሺህ፣ ኦሮሚያ 210 ሺህ እንዲሁም ትግራይ 50 ሺህ ተሳታፊዎችን ማስተናገዳቸው ታውቋል፡፡ የሌሎች ክልሎች የተጠቃለለ መረጃ አልደረሰም፡፡

በመሆኑም በሳምንቱ ከቲሸርት እና ከቦንድ ሽያጭ የተሰበሰበው ገንዘብ 44 ሚሊዮን ብር ደርሷል፡፡

የህዳሴው ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ ፐሮግራም በእግር ኳስ ጨዋታዎችም የሚቀጥል ሲሆን ከመጋቢት 14 እስከ 16 የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ልዩ የቦንድ ሽያጭ ሳምንቱ ነገ የሚጠናቀቅ ሲሆን በክልሎች ጥያቄ ሊራዘም እንደሚችል ታውቋል፡፡

አዝመራው ሞሴ