Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከልዩ ቦንድ ሽያጭ ሳምንቱ 40 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ተሰበሰበ

0 406

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከየካቲት 20 እስከ 29 በተካሄደው የልዩ ቦንድ ሽያጭ ሳምንት 40 ሚሊየን 212 ሺህ ብር መሰብሰቡን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

በሳምንቱ ከቦንድ ሽያጩ በተጨማሪ ከልገሳ 948 ሺህ ብር ተገኝቷል።

በልዩ ቦንድ ሸያጭ ሳምንቱ የተፈጠረው የህዝብ ንቅናቄ ከተጠበቀው በላይ እንደነበር የገለፀው ፅህፈት ቤቱ፥ ሽያጩ ከ50 ብር ጀምሮ የተካሄደ በመሆኑ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ እንደነበር አመላክቷል።

ቢንሻንጉል ጉምዝ፣ አፋር፣ ጋምቤላ እና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች የቦንድ ሽያጩን ዘግይተው በመጀመራቸው ቀኑን አራዝመውታል።

በአማራ፣ ደቡብ፣ ትግራይ እና ሀረርም የቦንድ ሽያጩ እየተጠናከረ የመጣበት ወቅት በመሆኑ ሽያጩ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ተብሏል።

በመሆኑም ሽያጩ ሲጠቃለል የገንዘቡ መጠን እንደሚጨምር ተገልጿል፡፡

በዚህ ሳምንት ለህዳሴው ግድብ ድጋፍ ከተካሄደው ሩጫ 21 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር እንደተገኘ መዘገቡ ይታወሳል።

ይህም ለህዳሴው ግድብ የሳምንቱን የድጋፍ መጥን ወደ 63 ሚሊየን ያደርሰዋል ብሏል ኢቢሲ በዘገባው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy