Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከአስር በላይ ፓርቲዎች በድርድሩ ሶስተኛ ወገን አደራዳሪ አያስፈልግም የሚል አቋማቸውን ገልጸዋል

0 463

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በ7ኛ ዙር ውይይታቸው በአደራዳሪ ጉዳይ ላይ ሁለት የተለያየ አቋም ይዘው ተከራክረዋል።

በውይይቱ መግባባት ባይችሉም፥ በ6ኛው ዙር ውይይት ሶስተኛ ወገን አደራዳሪ ያስፈልጋል የሚል አቋም ይዘው የነበሩ ፓርቲዎች አቋማቸውን ቀይረው ቀርበዋል።

በኢህአዴግ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የሚደረጉ ድርድሮች፥ በ3ኛ ወገን አደራዳሪ ይመሩ አይመሩ በሚለው ጉዳይ ላይ ለሁለት ተከፍለው ታይተዋል።

ኢህአዴግ፣ ቅንጅት፣ አንድነት እና አዲስ ትውልድ ፓርቲን ጨምሮ ከአስር በላይ ፓርቲዎችን የያዘው ስብስብ፥ ድርድሩ በራሳቸው በፓርቲዎች በዙር መመራት ይችላል የሚል አቋማቸውን በማንጸባረቅ ሶስተኛ ወገን እንደማያስፈልግ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኤዴፓ እና መኢአድን ጨምሮ በአንድ የተሰባሰቡት ስድስት ፓርቲዎች፥ ካሁን ቀደም በያዘው አቋሙ በመፅናት ሶስተኛ ወገን አደራዳሪ የግድ ነው ብሏል።

በአደራዳሪ ጉዳይ ላይ ለሁለት የተከፈሉት ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሌላ ውይይት ቀጠሮ ይዘው ተለያይተዋል።

የመላው ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ከአሁን በፊት በያዘው አቋሙ በመፅናት ሶስተኛ ወገን አደራዳሪ አያስፈልግም የሚለውን አቋሙን ደግሞ ገልጿል።

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በበኩሉ ድርድሩ በፓርቲዎች በዙር ወይም ከፓርቲዎች በሚመረጡ ይመራ የሚለው የመጨረሻ አቋሙ መሆኑን አስታውቋል።

የገዳ ስርአት አራማጅ ፓርቲ የሶስተኛ ወገን አደራዳሪ መኖር አለመኖር አጀንዳዎችን መሰረት አድርጎ ይወሰን፤ እንደ አጀንዳዎቹ በሶስተኛ ወገን አልያም በፓርቲዎች በዙር ልንደራደር እንችላለን ብሏል።

የሶስተኛ ወገን አደራዳሪ አያስፈልግም ያሉት ፓርቲዎች ሰላማዊ በሆነች ሀገር በሰላማዊ ፓርቲዎች መካከልየሚደረግ ድርድር ሰላምን ባጡ ሀገራት እንደሚደረገው አይነት በሶስተኛ ወገን የሚደረግ ድርድር አያስፈልግም፤ ማንም ሰው ከፖለቲካ አስተሳሰብ ነፃ እና ገለልተኛ ይሆናል ብለን ስለማናስብ ገለልተኛ እና ነፃ አደራዳሪ የሚለውን አንቀበለውም፤ አደራዳሪው መድረክ ከመምራት ባሻገር ሌላ ሚና ስለማይኖረው አያስፈልገንም የሚል ምክንያት አቅርበዋል።

ሶስተኛ ወገን አደራዳሪ ያስፈልጋል የሚሉት ስምንት ፓርቲዎች ደግሞ ነፃ እና ገለልተኛ ስንል የፓርቲ አባል ያልሆኑ ግለሰቦች ማለታችን ነው፤ ስለዚህ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ሊያደራድሩን ይገባል፤ ኢህአዴግን ስለማናምነው ሶስተኛ ወገን አደራዳሪ ወገን እንዲኖር እንፈልጋለን የሚል ምክንያት አቅርበዋል።

ኢህአዴግ በበኩሉ ከአሁን ቀደም ያለ ሶስተኛ ወገን አደራዳሪ በፓርቲዎች ብቻ በተደረጉ ድርድሮች የምርጫ ህጎች መሻሻላቸውን በማንሳት አንድ ግለሰብ የፓርቲ አባል አይደለም ማለት የሆነ አስተሳሰብ ደጋፊ ነው ማለት ስላልሆነ ገለልተኛ እና ነጻ አደራዳሪ የሚለውን ሀሳብ አልቀበልም ብሏል።

3ኛ ወገን አደራዳሪ ያስፈልጋል ያሉት ኢዴፓ እና ሰማያዊ ፓርቲን የያዘው የስድስቱ ፓርቲዎች ስብሰብ የመመካከሪያ ጊዜን ጠይቋል።

በመጨረሻም ፓርቲዎቹ በአደራዳሪ እና ሌሎች የድርድር እና ክርክር አሰራር ረቂቅ ደንብ ነጥቦች ላይ ለመምከር በመጭው ሚያዚያ 2 ቀን 2009 ዓ.ም ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘዋል።

ፓርቲዎቹ ከአሁን በፊት ባካሄዷቸው ውይይቶች የድርድሩ አላማ ላይ መስማማታቸው ይታወሳል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy