Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከወቅቱ 5 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገራት ኢትዮጵያ 2ኛ ሆናለች

0 1,133

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አፍሪካን ክራድል የአህጉሪቱ ሀገራት የተፅዕኖ ፈጣሪነት ደረጃ በየጊዜው ያወጣል፡፡

ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት የተፅዕኖ ፈጣሪነት ደረጃ መሰረት ደቡብ አፍሪካ ያለፈውን ጊዜ ደረጃ ስታስጠብቅ ኬንያ ከፍተኛ መሻሻል አድርጋለች፡፡

ናይጄሪያ እና አልጄሪያ በደረጃው ወረድ ብለው ታይተዋል፡፡ (BIG 5 AND THE NEWCOMERS) በሚል የወጣው መረጃ እንዲህ ቀርቧል፡፡

1 SOUTH AFRICA

ደቡብ አፍሪካ የዳበረ የኢኮኖሚ መሰረት የገነባች፤ብቸኛዋ የጂ20 እና ብሪክስ ሀገራት (ብራዚል፤ሩሲያ ፤ህንድና ቻይና አባል ሀገር እንደሆነች ይታወቃል፡፡

ደቡብ አፍሪካ የአውሮፓ ህብረት 10ኛዋ ስትራቴጂክ አጋር እና ከፍተኛ የንግድ ሸሪክ መሆኗ እንዲሁም የነፃነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ አለም አቀፍ እውቅና እና ሌሎችም ተደምረው ሀገሪቱ ተፅዕኖ ፈጣሪነቷ እንዲጎላ አድርጓል፡፡

2ETHIOPIA
ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በአለም እጅግ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ከሚያስመዘግቡ ሀገራት አንዷ እንደሆነች እየተዘገበ ነው፡፡

ከዚህም በሻገር ስሟ በመፅሀፈ ቅዱስ ውስጥ 44 ጊዜ የተፃፈ፤የሚያኮራ ረጅም ታሪክ ያላት፤በቅኝ ያልተገዛች፤ጠንካራ ወታደራዊ አቅም፤እንዲሁም ስኬታማ የዲፕሎማሲ ሚና የተጎናፀፈች መሆኑ በአህጉር እና በአለም ተቀባይነቷ ከፍ እንዲል አድርጓል በዚህም የሁለተኝነት ስፍራ አግኝታለች፡፡

የራሷ የቀን መቁጠሪያ፤ ፊደል ባለቤት እና ሌሎችም ብዙ ልዩ የሚያደርጋት መገለጫዎች ያሏት ሀገር ነች፡፡

3 EGYPT
ግብፅ በምድራችን ጥንታዊ ከሚባሉ ጥቂት ሀገራት አንዷ ነች ፡፡
ግብፅ ከእንግሊዝ እኤአ 1953 ነበር አልጄሪያ፤ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ቀድማ ነፃነቷን ያገኘችው፡፡

ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ጠንካራ ወታደዊ አቅምና የቱሪስት መስህብ በሆኑት ፒራሚዶቿም ትታወቃለች፡፡

4 KENYA
ጎረቤት ኬንያ በሰው ሀብት ካፒታል ትታወቃለች፡፡በአህጉሪቱ በርካታ የተማረ የሰው ሀይል ያፈራች እና በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በፈጣን ግስጋሴ ላይ መገኘቷ በአፍሪካን ክራድል 4ኛ ደረጃ አግኝታለች፡፡

በቅርቡ በወጣ ሪፖርት ለኑሮ ምቹ፤እያደገ ያለ መሰረተ ልማት እና በጠፈር ሳተላይት በኩል እየሰራች ያለው ስራም አስወድሷታል፡፡
5 MOROCCO

ሞሮኮ በአለም አቀፍ ኩባንያዎች ተመራጭ ሀገር እንደሆነች ዘገባው ያስረዳል፡፡

ለአውሮፓ አህጉር የምትቀርብ ሀገር በመሆኗም ከገበያ አንፃር ተጠቃሚ ያደርጋታል፡፡

ከሌሎች ጎረቤት የሰሜን አፍሪካ ሀገራት ጋር ስትነፃፀር የተረጋጋ ሰላም እና ፀጥታ ያለባት ሀገር ያደርጋታል፡፡ሌሎች 6-10 የተቀመጡ ሀገራት-
6.ናይጄሪያ
7.ዩጋንዳ
8.ሩዋንዳ
9.ዚምባቡዌ እና አልጄሪያ፡፡
ምንጭ፡አፍሪካን ክራድል.ኮም

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy