Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኮማንድ ፖስቱ የተወሰኑ ክልከላዎችን አነሳ

0 460

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከወጡ መመሪያዎች ላይ ከተቀመጡ ክልከላዎች የተወሰኑትን አነሳ፡፡የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በሰጡት መግለጫ  በመሰረተ ልማት፣ በፋብሪካዎች እና መስል ተቋማት አካባቢ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ከተፈቀደለት ሰራተኛ በስተቀር ማንኛውም ሌላ ሰው እንዳይንቀሳቀስ እንዲሁም በተቋማቱ አካባቢ የተላለፈው የሰዓት እላፊ ዛሬ በተላለፈው የአፈጻፅም መመሪያ ቁጥር 3 መሰረት ተሽሯል፡፡

ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማንኛውንም ሰው በቁጥጥር ስር ማዋል፣ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብርበራ ማድርግ፣ በሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ጽሑፍ፣ ምስል፣ በፎቶ ግራፍ፣ ቴያትር እና በፊልም የሚተላለፉ መልዕክቶችን ለመቆጣጠር እና ለመገደብ የወጣው እገዳም ተሽሯል ብለዋል፡፡የተዘረፉ ንብረቶች በመፈተሽ ለባለቤቶቹ እንዲመለሱ ማድረግ እና የመሳሰሉ እርምጃዎችም በመመሪያ ቁጥር ሶስት ተሽሯል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት እና የመከላከያ ሚንስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በመግለጫቸው አብዛኞቹ ክልከላዎች እንዲነሱ የተደረገው በአሁኑ ጊዜ የአገሪቱ ሰላም ወደ ነበረበት የተረጋጋ ሁኔታ እየተመለሰ በመሆኑ ነው ብለዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy