የዚምባቡዌ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህፃናት በትምህርት ቤትም ይሁን በቤታቸው አካላዊ ጥቃት እንዳይፈፀምባቸው ሲል አግዷል።ውሳኔው የመጣው የ1ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው የ6 ዓመት ልጅ በመምህሯ መገረፏን ተከትሎ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባት የተማሪዋ እናት በማመልከቷ ነው።ሊናህ ፉንጋዋ የተባለችው እናት እንደተናገረችው፥ ልጇ የተገረፈችው የቤት ስራዋን መስራቷን የሚያረጋግጥ ፊርማ በደብተሯ ላይ ወላጆቿን ባለምስፈረሟ ብቻ ነው ብላለች።ይህንኑ ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ይዛ ያመራቸው እናት ከልጇም አልፋ ለሀገሪቱ ልጆች ተፍራለች እየተባለ ነው።ይህም የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ከዚህ በኋላ ህፃናትን መግረፍ ክልክል ነው የሚል ውሳኔን በማሳለፉ ነው።ፍርድ ቤቱ ያሳለፈውን ክልከላም በዚምባቡዌ ህገ መንግስታዊ ችሎት ማረጋገጫ እስኪሰጠው እየተጠበቀ ነውውሳኔውም ወላጆች ልጆቻቸውን ለዘመናት ሲቀጡበት የመጡትን ባህል የሚቀይር ነው ተብሏልየተወሰኑ ወላጆች የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ላይ ሲሆኑ፥ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በበኩላቸው ውሳኔው ትክክል ነው እያሉ ነው። ምንጭ፦ ቢቢሲ