DEVELOPMENT

የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምርቱን ወደ ውጪ መላክ ሊጀምር ነው

By Admin

March 04, 2017

በሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ፋብሪካዎች እስከ መጋቢት ወር መጨረሻ ምርታቸውን ወደ ውጭ መላክ ይጀምራሉ ተባለ።የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር በላቸው ፍቅሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ የፓርኩን እንቅስቃሴ በአሁኑ ፍጥነት ማስኬድ ከተቻለ የታቀደውን የአንድ ቢሊየን የውጭ ምንዛሪ ማሳካት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡ዶክተር በላቸው እንዳመለከቱት በፓርኩ የማምረቻ ፋብሪካ ህንፃዎችን ወደ 52 ከፍ የሚያደርግ ተጨማሪ 15 አዳዲስ ሸዶች እየተገነቡ ነው።በፓርኩ ስራ ከጀመሩ ባለሃብቶች መካከል የታል ጨርቃጨርቅ ኩባንያ የኮሚዩኒቲና ኮሙዩኒኬሽን ማናጀር አቶ ሌላዓለም ተጫነ፥ ድርጅታቸው በፓርኩ ውስጥ የሚያመርተውን ሸሚዝ በመጋቢት ወር መጨረሻ ወደ አሜሪካ መላክ እንደሚጀምር ገልጸዋል፡፡አሁን ላይ 200 ዜጎችን ቀጥሮ እያሰራ የሚገኘው ኩባንያው በቀጣይ እስከ 4 ሺህ 500 ሰዎችን እንደሚቀበልም ጠቅሰዋል፡፡ምንጭ፦ ኢዜአ