የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ነገ በመቀሌ ከተማ ይጀመራል፡፡የማዕከላዊ ኮሚቴው ጽህፈት ቤት ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጸው ስብሰባው ባለፉት ስድስት ወራት በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ የነበሩ አፈፃፀሞችን ይገመግማል፡፡በህወሓት ጽህፈት ቤት መነሻ ሀሳብ የሚቀርብ የቀጣይ አስር ዓመታት የአቅም ግንባታ ስትራቴጂና ግብ ላይ በመወያየት ይፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡