Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የህዳሴው ግድብ ዘላለማዊ ሃውልታችን ነው- ዶክተር ሂሩት

0 549

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የዛሬ ማንነታችንን የሚመሰክር ዘላለማዊ ሐውልት መሆኑን  የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሒሩት ወልደማርያም ተናገሩ።የግድቡ ግንባታ የተበሰረበትን 6ኛ  ዓመት ምክንያት በማድረግ ከቴድሮስ  እስከ መስቀል አደባባይ ”የአባይ ቀን” የጎዳና ላይ ትርኢት ተካሂዷል።

በትርኢቱ ላይ የመከላከያና ፌደራል ፖሊስ፣የሴቶች ፌደሬሽን፣ አዲስ አበባ ወጣቶች ማህበርና ተማሪዎች የሰልፍ ስነ ስርዓት አካሂደዋል።በመስቀል አደባባይም የግድቡ ግንባታ የመጣበትን ሂደትና የደረሰበትን ደረጃ የሚያስቃኝ የፎቶ አውደ ርዕይ ተጎብኝቷል።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሒሩት ወልደማርያም በዚሁ ጊዜ እንዳሉት  ”የታላቁ ህዳሴ ግድብ የዛሬ ማንነታችንን የሚመሰክርልን  ዘላለማዊ ሀውልት በመሆን በዓለም አቀፍ መድረኮች ገጽታችንን እየገነባ ያለ ፕሮጀክት ነው።”

ግድቡ መጪው ትውልድ የሚወርሰው ህያው ቅርስ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሯ ግድቡ ተገንብቶ ለውጤት እንዲበቃ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተባበረ ክንድ መቆም አንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።  ”ግድቡን ኢትዮጵያዊያን ቢሰሩትም ለአፍሪካ እንደ ሌሎች ቅርሶች ኩራት በመሆን የትብብር መቀነት ይሆናል” ብለዋል። ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝን በጋራ የመጠቀም መርህን የምትከተል በመሆኗ ግድቡ የሠላምና የትብብር መሰረት እንደሚሆን ተናግረዋል።ዛሬ የተካሄደው ትርኢትም ግድቡ ከፍጻሜ እንዲደርስ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳዩበት መሆኑን የገለጹት ዶክተር ሂሩት ግድቡ የታለመለትን ግብ እንዲያሳካ ዜጎች ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታገል ቀኑብህ በበኩላቸው በግድቡ ዙሪያ የህዝቡ ንቅናቄ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናረዋል።

ኅብረተሰቡ ግድቡ ከተጀመረበት 2004 ዓ.ም አንስቶ በቦንድ ግዥ፣ በገንዘብ ስጦታና በጉልበት  ጠንካራ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

ከትርኢቱ ተሳታፊዎች መካከል የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ አስቴር አሰፋ ”ግድቡን ሄጄ ጎብኝቻለሁ የደረሰበት ደረጃም የሚያረካ ነው” ብለው በሴቶች ማህበር በኩል ቦንድ በመግዛት የግድቡን ግንባታ እየደገፉ መሆኑን ተናግረዋል።

ግድቡ ለመጪው ትውልድ ትልቅ ተስፋ መሆኑን ጠቁመው ኅብረተሰቡ የግድቡ ግንባታ እውን እንዲሆን መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት መክፈል ይኖርበታል ብለዋል።

ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የመጣው ወጣት ጌቱ በላይ በበኩሉ ”ለግድቡ ያለኝን አጋርነት ለመግለጽ በጎዳና  ትርኢቱ ላይ ተገኝቻለሁ” ብሏል።

”ፕሮጀክቱ ከጨለማ ወደ ብርሃን የሚወስደን ትልቅ አገራዊ ፋይዳ ያለው ፕሮጀክት ነው” ያለው ወጣት ጌቱ ለግድቡ ግንባታ ገቢ ከደሞዙ መቶ ፐርሰንት እንዲቆረጥ ማድረጉንና ግድቡ እስኪጣናቀቅ ድረስ ድጋፉን እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

ፕሮጀክቱ የዜጎችን ይህወት ወደ ተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር በመሆኑ ዜጎች በሚችሉት ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy