ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ እና ሱዳን ህዝቦች የጋራ ብልጽግና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የሱዳን ፓርላማ አባላት ተናገሩ፡፡
በሱዳን ፓርላማ የደህንነት ኮሚቴ ልኡካን ቡድን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ቡድኑ ከአፈጉባኤው ጋር በነበረው ቆይታ ሁላቱ አገራት የጀመሩትን የልማት ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር አቻ ፓርላማዎች ሊኖራቸው ስለሚገባ ሚና መክሯል፡፡ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግደብን በአካል ተገኝተው የመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው የተናገሩት የልኡካን ቡድኑ አባላት በኢትዮጵያ እያደረጉት ያለው ጉብኝትም የሁለቱንአገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው ግድቡ ሁለቱንም አገራት ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ሊደግፉት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የሁለቱን አገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከርም አቻ ፓርላማዎቹ በጋራ ሊሰሩ ይገባል ማለታቸውን የህዝብ ተወካዮች መክር ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬስን ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡