Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የመንግሥት ሥልጣን ከህዝብና አገር መለወጫነት ይልቅ

0 422

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የመንግሥት ሥልጣን ከህዝብና አገር መለወጫነት ይልቅ የግል ጥቅም ማራመጃ ለማድረግ የሚካሄድ ጥረት ና ሥልጣንን ካለአግባብ ለመጠቀም የመሻት ዝንባሌ በቸልታ ከታየ ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳት ጠቅላላ ውድመት እንደሚሆን በመገንዘብ ከውስጣችን በትግል ማስወገድ ይገባናል፡፡

በያዝነው ሥልጣን ህዝብና አገርን ከመለወጥና ከማሳደግ ውጭ ለግል ጥቅም የሚስገበገቡ ሰዎችን በፅናት መፋለም ይገባል፡፡ በምግባረ ብልሹነትም ሆነ በስንፍና የመንግሥት ሥልጣንን የህዝብና የአገር መለወጫ መሣሪያ አለማድረግ ሁላችንን በተለይ ደግሞ ብዙሃኑን ህዝብ ከባድ ዋጋ የሚያስከፍል እንደሚሆን በመገንዘብ እነዚህን አፍራሽ አዝማሚያዎች አጥብቆ መታገልና ማሸነፍ ይገባል፡፡ አለአግባብ ለመጠቀም የሚደረግና ዛሬም እንደትላንቱ ይህን ዝንባሌ በህዝብ አጀንዳ ለመሸፈን የሚደረግ ማንኛውም የጥፋት ሩጫ በፅናት መፋለም ይገባል፡፡

ከላይ በዝርዝር የተቀመጡትን የትግል ስልቶች አቀናጅተን በብቃት ከፈፀምን የአገራችን ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ ጉዞ አንገት ያስደፋቸው የትላንት አስተሳሰቦች የአገራችንንና የህዝባችንን ብሩህ እድል ለአደጋ እንዳያጋልጡ ማድረግ እንችላለን፡

ቀጣይነት ባለው ትግል የጀመርነውን የህዳሴ ጉዞ በማጠናከር የበለፀገች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን እንደምናደርግ ለአፍታ ቢሆን አንጠራጠርም፡፡ ወሳኙ ነገር በጥብቅ ዲሲኘሊን የመታገልና የህዝብን ጥቅም የማስቀደም ጉዳይ ነው፡፡ Ewnetu Bilata Debela

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy