የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ያቀረበውን ሪፖርት አዳምጧል። በአሁኑ ወቅት አገሪቷ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ሆናና የዚህን አዋጅ አፈጻጸም የሚመረምረው ቦርድ ሪፖርቱን ሲያቀርብ፤ ከ547 የምክር ቤቱ አባላት ውስጥ የተገኙት 335 ብቻ ናቸው። የተቀሩት 242 አባላት በትናንትናው ስብሰባ እንዳልተገኙ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል። ለመሆኑ 242 አባላቱ ከዚህ የበለጠ ምን አስቸኳይ ጉዳይ ገጥሟቸው ይሆን ?