Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የሞጆ ሃዋሳ የፍጥነት መንገድ የአስፓልት ንጣፍ ስራ ተጀመረ

0 1,678

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵየ መንገዶች ባለስልጣን 56 ነጠብ 4 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የመንገዱ የአስፓልት ንጣፍ በተያዘለት ጊዜ እንዲጣናቀቅ ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

ተቋራጩና አማካሪ ድርጅቶቹም ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም መንገዱ በተያዘለት ጊዜና የጥራት መስፈርት ይጠናቀቃል ብለዋል።

መንገዱ አዲስ አበባን ከሀዋሳ የሚያስተሳስር መንገድ ሲሆን፥ ሀገሪቱ በሁለተኛው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ለመገንባት ያቀደቺው 350 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ አካል ነው።

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ ሞያሌ ናይሮቢ ሞምባሳ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን ያካተተ ነው።

በአራት ክፍሎች ማለትም ከሞጆ መቂ፣ ከመቂ ዝዋይ፣ ከዝዋይ አርሲ ነገሌና ከአርሲ ነገሌ ሃዋሳ የፍጥነት መንገድ ወስጥ የሶስቱ ግንባታ ከወራት በፊት መጀመሩ ይታወሳል።

ከዚህ ውስጥ ደግሞ የሞጆ ሃዋሳ የፍጥነት መንገድ ቁጥር አንድ አካል የሆነው የሞጆ መቂ መንገድ የአስፓልት ስራው የተጀመረ ሲሆን፥ መንገዱ በሶስት ዓመት ተኩል እንዲጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የባለስልጣኑ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ ገልጸዋል።

መንገዱ ከአፈረ ቆረጣ እና ጠረጋ በተጓዳኝ 3 ነጥብ 6 ኪሎሜትሩ አስፓልት ለብሷል፤ ለሙሉ ንጣፉም ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተይዞለታል።

የመንገዱ ግንባታ ትላልቅ የድልድይ ግንባታዎች፣ማሳለጫዎችና ማቋረጫዎች፣ የአቃፊ ግንብ፣ የመንገድ ዳር የትራፊክ
ምልክቶችና ሌሎች ስራዎችን አካቶ የሚገነባ ነው።

ይህ መንገድ ከሞጆ ሃዋሻ ብቻ የሚገነባ ሳይሆን ከአዲስ አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድ ጋር የሚተሳሰር መንገድን ጨምሮ የአገናኝ መንገዶችን ግንባታ ያካተተ ነው።

የስራ ተቋራጩ ዋና መሃንዲስ ሰን ጂያንግሎ፥ መንገዱን በተያለዘት ጊዜ፣ ወጪና መስፈርት አሟልተን እንሰራለን ብለዋል።

አካባቢው ለመንገድ ግንባታ ምቹ ሲሆን ከካሳና ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ችግሮች የመንገዱን ግንባታ እንዳያጓትቱ፥ አስፈላጊው ጠንቃቄ መደረጉን ደግሞ አቶ ሳምሶን ያነሳሉ።

አቶ ሳምሶን እንደሚሉት በርካታ ወጣቶች በዚህ ፕሮጀክት ላይ እየተሳተፉ ሲሆን፥ ከስራ ባለፈም ልምድና እውቀት እያገኙ መሆኑን ያነሳሉ።

ወጣቶቹ አሁን ላይ በአካባቢያቸው የሚዘረጋው መሰረተ ልማት ተጨባጭ ተስፋን እንደሰነቀላቸው ገልፀው፥ መንገዱን ተከትለው ግብርና እና ንግድን አጣምሮ ለመስራት ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡

የሞጆ ሃዋሳ የፍጥነት መንገድ ሲጠናቀቅ ወደ ሃዋሳና ሌሎች ከተሞች በፍጥነት ለመድረስ ከማስቻሉም በላይ አዳዲስ የንግድ ከተሞች እንዲፈጠሩ ያደርጋል።

አሁን ላይም የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጨምሮ በርካታ አዳዲስ ተቋማት ስላሉ ምርቶችን ከፋብሪካዎች ወደ ገበያ፥ ጥሬ
ዕቃዎችን ደግሞ ከአርሶ አደሮች ማሳ ወደ ፋብሪካዎች በፍጥነትና በምቾት እንዲመላለስ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy