NEWS

የርቀት ትምህርት ላይ የሚታዩ የህግ ጥሰቶችን የሚያስቀር ረቂቀ መመሪያ ተዘጋጀ

By Admin

March 09, 2017

በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የርቀት ትምህርት ላይ የሚታዩ የህግ ጥሰቶችን ለማስቀረት ረቂቀ መመሪያ ተዘጋጀ።

መመሪያው የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በዘጋጀው እና የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮችና በተሳተፉበት መድርክ ውይይት ተካሂዶበታል።

መመሪያው ከኤጀንሲው ፈቃድ ሳያገኙ ስራ የጀመረ የትምህርት ተቋም ያለምንም ማስጠንቀቂያ እንዲዘጋ የሚል ድንጋጌን በውስጡ ይዟል።

እንዲሁም ለአምስት አመታት በከፍተኛ ትምህርት ስራ እንዳይሰማራ እሰከ መከልከል የደረሱ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው።

በመድረኩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማሳደግ ያገዛል የተባለ የጥራት መቆጣጠሪያ የጋራ ሰነድም ቀርቧል። FBC