Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የስዊዘርላንዱ ኔስሌ በኢትዮጵያ ፋብሪካ የመክፈት ሀሳብ እንዳለው ይፋ አደረገ

0 724

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የስዊዘርላንዱ ኔስሌ ኩባንያ፣ በኢትዮጵያ በወተት ማቀነባበር መስክ ፋብሪካ የመክፈት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።

የኔስሌ የወደፊት የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከሆኑ 20 አገሮች ውስጥ እንዲሁም ከአምስት አቅም ያላቸውና ምርጫው ካደረጋቸው አገሮች ተርታ ኢትዮጵያ ትካተታለች።

በኢኳቶሪያል አፍሪካ ቀጣና የኔስሌ የአፍሪካ ቀንድ ክላስተር ማናጀር የሆኑት አቶ ወሰንየለህ ፍቅሬ፥ በኢትዮጵያ ወደፊት እንደሚገነባ የሚጠበቀው የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ መቼ ዕውን ሊሆን እንደሚችል የሚወስኑት በአገሪቱ የሚገኘው የወተት ምርትና የአቅርቦት መጠን፣ የወተት ጥራት ደረጃና ጤንነት እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

ይሁንና የፋብሪካው ምሥረታ መቼ ሊሳካ እንደሚችል ገና ያልታወቀ ሲሆን፥ ከዚህ ይልቅ የዱቄት ወተት ምርቶቹን እዚሁ ለማሸግ የሚያበቁትን ዝግጅቶች በማድረግ ይህንን የሚያከናውን ፋብሪካ መመሥረቱ እንደማይቀር አረጋግጠዋል።

የማሸጊያ ፋብሪካው በቅርቡ ዕውን ሊሆን እንደሚችል ቢገለጽም፣ በምን ያህል ጊዜ ውስጥና በምን ያህል ወጪ ለሚለው ምላሹ ወደፊት እንደሚታወቅም አስታውቀዋል።
ከዚህ ባሻገር ኔስሌ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴን የምርቱ አምባሳደር አድርጎ መሰየሙ ይፋ ተፈርጓል፡፡

በመላው ዓለም ከ2 ሺህ በላይ ብራንዶችን የሚያስተዳድረው ኔስሌ፣ ከ10 ሺህ በላይ ምርቶችን በማምረት ከ1 ቢሊየን በላይ የምርት ሽያጭ የሚያከናውን የምግብና የመጠጥ አምራች ኩባንያ ነው።

በአብዛኛው በውኃ፣ በወተት፣ በቡና እንዲሁም በልዩ ልዩ የበለፀጉ ምርቶቹ የሚታወቀው ኔስሌ፣ በኢትዮጵያ የውኃ ማዕድን መስክ ከአገር ውስጥ አምራቾች ጋር አብሮ ለመሥራት መስማማቱ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy