ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ እ.ኤ.አ በ2011 የግብፅ አብዮትን ተከትሎ ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በግድያና በሌሎች ወንጀሎች ተከሰው የእድሜ ልክ እስራት ተበይኖባቸው ነበር፡፡
ሙባረክ በደቡባዊ ካይሮ በቁም እስር ላይ ሆነው ህክምና ይከታተሉበት ከነበረው ወታደራዊ ሆስፒታል ወጥተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ማምራታቸውን ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡
የ88 ዓመቱ የእድሜ ባለፀጋ ሆስኒ ሙባረክ እ.ኤ.አ 1981 ፕሬዝዳንት አንዋር ሰዳት መገደላቸውን ተከትሎ ነው በመፈንቀለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት፡፡
ይሁንእንጂ በሆስኒ ሙባረክ የስልጣን ዘመን የደህንነት ኃላፊ የነበሩትና የአሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ሲሲ ሙባረክ እንዲለቀቁ ለዘብተኛ በመሆናቸው ነው የተፈቱት በሚል ወቀሳ እየቀረበባቸው ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ሲሲ ከሆስኒ ሙባረክ ስልጣን መገርሰስ በኃላ በምርጫ ወደስልጣን የመጡትን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሙሃመድ ሙርሲን ለእስር ዳርገው ከነ ግበረ አበሮቻቸው የሞት ፍርድ ድረስ ተፈርዶባቸው ወደ እድሜ ልክ እስር ተቀይሮላቸው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ለ18 ቀን በቆየው በ2011ዱ የግብፅ አብዮት ሆስኒ ሙባረክ ከኃላፊነት ራሳቸውን እስካነሱበት ጊዜ ድረስ በመላ አገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች ለተቃዋሙ አደባባይ የወጡ 800 ግብፃዊያን መገደላቸውን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል፡፡