Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የቀድሞ ፍቅረኛውንና ሌሎች ሁለት ሰዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ

0 861

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአዲስ አበባ ልዩ ስፍራው 22 ማዞርያ አካባቢ የቀድሞ ፍቅረኛውን ከሌላ ወንድ ጋር ለምን አይሻለሁ በማለት እርሷንና ሌሎች አብረዋት የነበሩ ሁለት ሰዎችን በጥይት ተኩሶ የገደለው ግለሰብ የእድሜ ልክ እስራት ተወሰነበት።

ተከሳሹ ኮንስታብል አውንቶ አለማየሁ ሲሆን የፌደራል ፖሊስ አባልና የ28 ዓመት ወጣት ነው።

ግለሰቡ ጥር 1 ቀን 2002 ዓ.ም በተለምዶ 22 ማዞርያ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የቀድሞ ፍቅረኛውን ምህረት ሀይለማርያም ከሌላ ወንድ ጋር ለምን አይሻለሁ በማለት ህብረተሰቡን እንዲጠብቅበት በተሰጠው ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ አራት ጥይቶችን በመተኮስ ህይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል በማለት ነው አቃቤ ህግ በ1ኛ ክስ የመሰረተበት።

የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሹ በዚህ ሳያበቃ አብሯት የነበረውን ሟች እንቢአለ መለሰውን
ጨካኝነትና አደገኝነትን በሚያሳይ መልኩ በአምስት ጥይቶች ተኩሶ በመግደሉም በ2ኛ ደረጃ አቃቤ ህግ ክስ መስርቶበታል።

ተከሳሽ ኮንስታብል አውንቶ አለማየሁ በዚህ ሳያበቃም አቃቤ ህግ በ3ኛ ክሱ ከሁለቱ የግል ተበዳዮች ጋር አብራ የነበረችውን የግል ተበዳይና ሟች ሀና ደስታን ጭካኔ በተሞላበት መልኩ አስቀድሞ በታጠቀው ክላሽንኮቭ የጦር መሳርያ በ10 ጥይቶች በመምታት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉም በክሱ ተብራርተቷል።

በዚህም መሰረት አቃቤ ህግ በግለሰቡ ላይ በከባድ የሰው ህይወት ማጥፋት ወንጀል ክስ መስርቶበታል።

ክሱን የተከታተለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት በግለሰቡ ላይ የተመሰረተውን የአቃቤ ህግን ክስ አድምጧል።

ፍርድ ቤቱም በተደጋጋሚ ለተከሳሹ ጥሪ ቢያደርግም ግለሰቡ መገኘት ባለመቻሉ በሌለበት መዝገቡ እንዲታይ ወስኗል።

ከሳሽ አቃቤ ህግም በተከሳሹ ኮንስታብል አውንቶ አለማየሁ ላይ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ አሰምቷል።

በዚህም ችሎቱ በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ በዛሬው የችሎቱ ውሎም ተከሳሹን በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል።

ፖሊስም ተከሳሹን ተከታትሎ በቁጥጥር ስር እንዲያውልና ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብ ትእዛዝ ሰጥቷል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy