Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኢንቨስትመንት የተሰማሩ የ27 ባለሃብቶችን ፍቃድ ሰረዘ

0 303

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኢንቨ ስትመንት ጽሕፈት ቤት የ27 ባለሃብቶችን የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰረዙን አስታወቀ። የ14 ባለሃብቶችን የልማት አቅም በመገምገም ከያዙት መሬት 50 በመቶ ያህሉን እንደቀነሰባቸው ገልጿል።

የክልሉ ኢንቨስትመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ጋሻው ሽሞ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፣ በ2008 .ም በጀት ዓመት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በ225 ፕሮጀክቶች ላይ ክትትል ተደርጓል። በዚህ መሰረትም 27 ባለሃብቶች በገቡት ውል መሰረት ኢንቨስትመንቱን ባለማከናወናቸውና አፈፃፀማቸው እጅግ ዝቅተኛ በመሆኑ የኢንቨስትመንት ፍቃዳቸው ሊሰረዝ ችሏል።

ፍቃዳቸው የተሰረዘባቸው ባለሀብቶችም ተረክበውት የነበረውን 10 384 ነጥብ ሰባት ሄክታር መሬት ተነጥቀው ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ መደረጉን የገለጹት ኃላፊው፣ ባለሃብቶቹ አስመዝግበው የነበረው የካፒታል መጠንም 138 ሚሊዮን 747 296 ብር እንደነበር አስታ ውሰዋል።

በክልሉ ይህ ዓይነት እርምጃ ሲወሰድ የመጀመሪያ እንዳልሆነ የገለፁት አቶ ጋሻው፤ በ2008 በጀት ዓመትም በተመሳሳይ የ90 ባለሀብቶች የኢንቨ ስትመንት ፍቃድ መሰረዙን ተናግረዋል።

በተመሳሳይም የ14 ሌሎች ባለሃብቶችን የልማት አቅም በመገምገም ከያዙት መሬት 50 በመቶ የይዞታ ቅነሳ እንደተደረገባቸው ኃላፊው አስታውቀዋል።በተጨማሪም ለ164 ባለሀብቶች ቀላልና ከባድ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን አቶ ጋሻው ጠቁመዋል።

ፍቃዱ ከተሰረዘባቸው ባለሃብቶች መካከል የተወሰኑትን አዲስ ዘመን ያነጋገረ ሲሆን፣ ባለሀብቶቹ ክልሉ የወሰደው እርምጃ በትክክለኛው መንገድ በተደረገ ግምገማ አለመሆኑን ተናግረዋል።

የዚህን ዘገባ ሙሉ

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy