Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ

0 443

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ባለፉት 6 ወራት በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ እና መደበኛ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ ወራት የመፍትሔ አቅጣጫ አስቀመጠ፡፡
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለምነው መኮነን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ብአዴን ባሳለፋቸው ሂደቶች ብዙ ውጤቶችን ያስመዘገበ ቢሆንም ሂደቱ ደረጃ በደረጃ ህዝቡን ከመምራት ብቃት አኳያ የአስተሳሰብ ድክመትና የአፈፃፀም ጉድለት አጋጥሞታል፡፡ በመሆኑም የተሀድሶው ንቅናቄ የአስተሳሰብ ችግሮችን በመፍታት ለሰላም፣ለልማትና ለመልካም አስተዳደር የተመቸ የአመራር አንድነትና መዋቅራዊ ለውጥ ሊያመጣ የሚያስችል እና የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄዎችን በአጭርና በመካከለኛ ጊዜ ለመፍታት ያለመ ንቅናቄ ነበር፡፡ በዚህም ማዕከላዊ ኮሚቴው የአስተሳሰብ ግልጽነትና የሃሳብ አንድነት በድርጅቱ አመራሮች ዘንድ መምጣቱን ገምግሟል፡፡ ይህ በመሆኑ ድርጅቱ ህልውናው ተጠናክሮ ህዝብን መምራት በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲገኝ የጥልቅ ተሀድሶው ንቅናቄ ትልቅ አቅም ፈጥሮለታል ብለዋል፡፡
አቶ አለምነው አክለውም ከጥልቅ ተሀድሶው በፊት በአንዳንድ አመራሮች ዘንድ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር ጐልቶ ይታይ ነበር፡፡ በዚህም የተጠረጠሩ 462 ከፍተኛ እና መካከለኛ እንዲሁም 362 የታችኛው አመራሮች ጉዳያቸው በመጣራት ላይ ያለ ሲሆን ከተጠሩት ጉዳዮች ውስጥ በ1ኛው ላይ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነቱ እንዲታገድ በሁለተኛው ላይ ከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው ማዕከላዊ ኮሚቴው ወስኗል፡፡ ከክልል ኃላፊዎች መካከል 16ቱ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ፣ 11ዱ ደግሞ ከደረጃቸው ዝቅ እንዲሉ ሆነዋል፡፡
በቀጣይ ብአዴን ህዝብ የመምራት ብቃቱ እንዲረጋገጥ ህዝብን የሚጠቅሙ አስተሳሰቦችን መያዝ፣የህዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ መረባረብ ፣ የግብርና ምርት እንዲያድግ ህዝብን ማነቃነቅ ፣ በከተሞች የአምራች ኢንዱስትሪ መስኮችን ማስፋት ፣ ህዝባዊ አገልግሎትና ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ድርጅቱ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡
አቶ አለምነው መኮነን በመግለጫቸው አያይዘውም በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሸ ተራ በሚባለው አካባቢ በመሬት መንሸራተት ምክንያት በተጐዱ ወገኖች የተሰማቸውን ሀዘን በድርጅቱ ስም ገልፀው ለቤተሰቦቻቸውና ለዘመዶቻቸው መፅናናትን¨ተመኝተዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy