Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የቦረና ባሊ ገዳ ርክክብ ስነ ስርዓት ተጠናቀቀ

0 1,186

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የገዳ ስርዓትን በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ አድርጎ ከማስመዝገብ ባለፈ የአሁኑ ትውልድ እንዲያውቀውና እንዲረዳው ለማድረግ በትምህርት ስርዓት ውስጥ ይገባል አሉ የኦሮሚያ ከልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ።

ለስምንት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 71ኛው የቦረና ባሊ ገዳ ርክክብ ስነ ስርዓት ዛሬ ተጠናቋል።

በዚህም ላለፉት ስምንት አመታት ሲመሩ የነበሩት 70ኛው አባ ገዳ ጉዮ ጎባ ለተተኪያቸው አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ኩራ አስረክበዋል።

71ኛው የቦረና አባገዳ በመሆን የተረከቡት አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ኩራ፥ ባለፈው አባ ገዳ ሲሰሩ የነበሩ መልካም ስራዎችን በማስቀጠል ህዝቡን የተሻለ ለማገልገል ቃል ገብተዋል።

መልካም ተግባራትን እንደሚያስፈጽሙ የተናገሩት አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ፥ የስርዓቱ ማስፈጸሚያ ቦታዎች ተጠብቀው እንዲቆዩ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በበኩላቸው፥ የገዳ ስርዓት የዴሞክራሲ ስርዓት ባልነበረበት ወቅት ዴሞክራሲ ማሳያ እንደነበር አንስተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ስርዓቱ ለቀጣዩ ትውልድ ይተላለፍ ዘንድም የክልሉ መንግስት ይሰራል ብለዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በመደበኛ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ገብቶ ትውልዱ እንዲያውቀው ለማድረግ ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የክልሉ መንግስት ከጅማ፣ ቡሌ ሆራ፣ ዲላ እና መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመሆን በስርዓተ ትምህርት ውስጥ ማካተት በሚቻልበት አግባብ ላይ እየሰራ ይገኛል።

1 ሺህ 375 አመት እንዳስቆጠረ በሚነገርለት የቦረና ገዳ ስርዓት ሶስት የተለያዩ ገዳዎች አሉ።

አርቦራ፣ ሃወጡ እና ኮኒቱ ሲሆኑ፥ አርቦራ አንጋፋውና አብዛኛው የገዳ አባቶች የሚወጡበት ገዳ ነው።

አዲሱ አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ኩራ 71ኛው አባ ገዳ ሲሆኑ፥ ለቀጣይ ስምንት አመታት የባሊ ገዳን ይመራሉ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy