Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የተስቲ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ባለቤትና ዋና ስራ ኣስኪያጅ ኣቶ ፋይሰል ዓብዶሽ ከ200000 ብር በላይ ወጪ በማድረግ 385 ኩንታል በቆሎ ገዝተው ኣስረከቡ !!

0 814

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የተስቲ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ባለቤትና ዋና ስራ ኣስኪያጅ የሆኑት ኣቶ ፋይሰል ዓብዶሽ ኣሁን በኢትዮ ሶማሊና በኦሮሞያ ክልሎች የተወሰኑ ኣከባቢዎች በድርቅ ምክንያት የተጎዱትን ወገኖቻችን ለመርዳት የሚያግዝ በራሳቸው ተነሳሽነት ከ200000 ብር በላይ ወጪ በማድረግ 385 ኩንታል በቆሎ ገዝተው ኣስረከቡ !! እንደሚታወቀው ከዓለም የኣየር ንብረት መዛባት ጋር በተያያዘ ኣሁን በኢትዮ ሶማሊ ክልልና በኦሮሞያ ክልል የተወሰኑ ኣከባቢዎች ድርቅ መከሰቱንና ከ5 ሚሊዮን የማያንስ ህዝብና ወገኖቻቸውና ጥሪቶቻቸው ለከባድ የምግብና የውሃ እጥረት መጋለጣቸውና መንግስት በድርቅ የተጎዱትን ወገኖቻችንና እንስሶቻቸውን ለመርዳት የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል።ሆኖም የድርቁ ስፋትና የተጎዱ ወገኖቻችን ብዛት ሲታይ ድጋፍ የማድረጉ ጉዳይ ለመንግስት ብቻ የሚተው ሳይሆን ሁሉ ኣቅም ያለው ኢትዮጵያዊ የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግ የሚያስገድድ ጉዳይ መሆኑ እሙን ነው። ይህንን ተከትሎም የተስቲ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ባለቤትና ዋና ስራ ኣስኪያጅ የሆኑት ኣቶ ፋይሰል ዓብዶሽ ለነዚህ ከዓለም የኣየር ንብረት መዛባት ጋር በተያያዘ ኣሁን በኢትዮ ሶማሊ ክልልና በኦሮሞያ ክልል የተወሰኑ ኣከባቢዎች በድርቅ የተጎዱትን ወገኖች ለመርዳት የሚያግዝ በራሳቸው ተነሳሽነት ከ100000 ብር በላይ ወጪ በማድረግ 185 ኩንታል በቆሎ ገዝተው በ09/07/09 ዓ/ም በተወካያቸው በኩል ለሶማሊ ክልል እርዳታ ማስተባበርያ ቢሮ በማስረከብ ዜግነታዊ ግዴታቸውን ተወቷል። በተጨማሪ ላይ ኣቶ ፋይሰል ዓብዶሽ በደርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን እንደዚህ ዓይነት ድጋፍ ሲያደርጉና ማህበራዊ ግዴታቸው ሲወጡ የመጀመርያቸው ኣይደለም።ከዚህ ቀደም በራሳቸው ሙሉ ወጪ ት/ቤት ገንብተው ለጉጂ ህዝብ ማስረከባቸው እንዳለ ሆኖ በቅርቡ የካቲት ወርም በኦሮሚያ ክልል በጊጂ ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የተጎዱትን ወገኖቻችን ለመርዳት ከ120000 ብር በላይ ወጪ በማድረግ 200 ኩንታል በቆሎ ገዝተው በኦሮሚያ ክልል ለሸኪሶ ዞን እርዳታ ማስተባበርያ ፅ/ቤት

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy