Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በእንፋሎት ኃይል ዘርፍ መሰማራት እንደሚፈልጉ ገለጹ

0 327

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በእንፋሎት ኃይልና በሴራሚክ ማምረት ስራዎች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ።ባለሃብቶቹ ዛሬ ከፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ጋር በፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ውይይት አድርገዋል።ባለሃብቶቹ በእንፋሎት ኃይል፣ በቆዳና ቆዳ ውጤቶች እንዲሁም በሴራሚክ ሥራ ላይ ለመሰማራት ነው ፍላጎት ያላቸው።

ቀደም ብሎ ኢትዮጵያ ለቱርክ ባለሃብቶች ያቀረበችው ማበረታቻና በሥራቸው ውጤታማ መሆናቸው መዋዕለ ንዋያቸውን ለማውጣት ለመፈለጋቸው በምክንያት ተጠቅሷል።

በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ፋቲህ ዩሉሶይ፥ ፕሬዚዳንት ሙላቱ በቱርክ ከወራት በፊት ያደረጉት ጉብኝት ባለሃብቶቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ካደረጉ ምክንያቶች ተጠቃሽ መሆኑን አውስተዋል።ፕሬዚደንት ሙላቱ ከቱርክ አቻቸው ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ጋር የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ለማጠናከር መስማማታቸው ይታወሳል።በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያና በቱርክ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 440 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል።

ይሁንና ይህን አሃዝ ወደ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከፍ ለማድረግ ሁለቱ አገሮች ተስማምተዋል።ቱርክ በምስራቅ አፍሪካ በ6 ቢሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ሥራ እያካሄደች መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደር ዩሉሶይ፥ ከዚህ ውስጥ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላሩ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ኢንቨስት መደረጉን ተናግረዋል።

ይህም በኢትዮጵያ ከ30 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠሩን ገልጸዋል።ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ በበኩላቸው፥ ባለሃብቶቹ በፈለጉት የኢንቨስትመንት ዘርፎች ቢሰማሩ ትርፋማ እንደሚሆኑ ነው የገለጹላቸው። ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy