Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የትራፕ የጉዞ ክልከላ ውሳኔ ዳግም በፍርድ ቤት ተሻረ

0 283

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሃዋይ የፌዴራል ፍርድ ቤት ትራምፕ በ6 አገራት የጣሉትን የጉዞ ክልከላ በድጋሚ ውድቅ ማድረጉ ተገለጸ፡ሀሙስ ምሽት ተግባራዊ እንደሚሆን ይጠበቅ የነበረው የትራምፕ የጉዞ እገዳ ውደቅ የተደረገው ለአገሪቱ ደህንነት ሲባል መሆኑን የአሜሪካ ዲስትሪክት ዳኛ ዴሪክ ዋትሰን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕም የዳኛውን ውሳኔ ከሚገባው በላይ የተጋነነ ነው በማለት አጣጥለዉታል፡፡ትራምፕ በ6  አገራት ጥለውት የነበረው የጉዞ ክልከላ ህግ ለ90 ቀናት እንዲሁም ለስደተኞች 120 ቀናት ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚከለክል መሆኑ ይታወሳል፡፡በጥር ወር ወጥቶ የነበረው ተመሳሳይ ህግ ግራ መጋባትንና ተቃውሞን በመፍጠሩ በሲያትል ዳኛ ውድቅ መደረጉ የሚታወስ ነው᎓᎓ምንጭ፤ ቢቢሲ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy