Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የትግራይ ክልል በኦሮሚያ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ አደረገ

0 600

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኦሮሚያ ክልል በድርቅ የተጎዱ የቦረና እና ጉጂ ዞን አርብቶ አደሮችን ለመደገፍ የትግራይ ክልል በ15 ተሽከርካሪዎች የተጫነ የእንሰሳት መኖ ድጋፍ በቦታው በመገኘት አስረክቧል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወይዘሪት ኡሚ አባጀማል፥ የትግራይ ክልል ላደረገው ድጋፍ አመስግነው፥ የሁለቱ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በጥሩ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም አጋጣሚ የሚቀጥል መሆኑን ክልሉ ያደረገው ድጋፍ ያሳያል ብለዋል።

 

የትግራይ ክልል ያደረገውን ድጋፍ ያስረከቡት የክልሉ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ጌታቸው ፈረደ በበኩላቸው፥ “ያደረግነው ድጋፍ በቂ ባይሆንም ሁሌም አብረናችሁ እንዳለን የሚያሳይ ነው” ብለዋል።

ከሳምንት በፊት የአማራ ክልል 5 ሺህ ኩንታል የምግብ እህል እና ሁለት የውሃ ቦቴ ተሽከርካሪዎችን ለኦሮሚያ ክልል ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy