NEWS

የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ የካርቦን ንግድ ፕሮጀክት የ68 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

By Admin

March 10, 2017

የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሁለት የካርቦን ንግድ  ፕሮጀክቶች የሚውል የ68 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን ገለፀ፡፡ባንኩ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ መርሃ ግብር  ማስተግበሪያ  በኦሮሚያ ክልል ለተመረጡ የደን ልማትና  ፕሮጀክቶች የሚዉል 68 ድጋፍ መሆኑ  አመለከቷል ፡፡መርሀ ግብሩ  በአከባቢው ማህበረሰብ ሊከናወኑ የሚችሉ እንደ  የደን ቱሪዝም  የመሳሳሉ ከአከባቢ ጋር ተስማሚነት ያላቸውን ስራዎቸ ለማስፋፋት እንደሚውልም ተገልጿል፡፡ኢትዮጵያ የደን ሽፋኗን በ30 በመቶ በማሳደግ እ.ኤ.አ በ2025 ከካርበን ጋዝ ልቀት ነጻ የመሆን ግብ እንዳላት የአለም ባንክ ዘገባ ያስረዳል፡፡በእንደነዚህ አይነት ፕሮጀክቶች በአገራት   ድህነትን  መቅረፍና የውጭ ቀጥታ እንቨስትመንትን   እንዲስፋፋ መደገፍ  የአለም ባንክ ተግባሩ መሆኑ በዘገባው ተገልጿል፡፡ይሁን  እንጂ የቅር  ግዜ  ጥናቶች  እንደሚያመለክቱት ለአየር ንብረት  ለውጥ መቋቋሚያ ቃል ከሚገባው ገንዘብ 10 በመቶ ያህሉ ብቻ ለአከባቢያዊ ፕሮጀክቶች መለቀቁ በተመሳሳይ  ፕሮጀክቶቸ  ላይ  ጥርጣሬን  የሚፈጥር እንዳይሆን ስጋት  ሆኗል፡፡ምንጭ፣ አፍሪካን ኢንሳይደር