NEWS

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በቆሸ በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ዜጎች ማቋቋሚያና ለሟች ቤተሰቦች ድጋፍ የሚውል የ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

By Admin

March 17, 2017

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በቆሸ በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ዜጎች ማቋቋሚያና ለሟች ቤተሰቦች ድጋፍ የሚውል የ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ በተለምዶ ቆሸ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በዜጎቻችን ላይ ድንገተኛ የአፈር መደርመስ አደጋ የክልሉ መንግስት ቀደም ሲል የተሰማውን ሀዘን መግለፁ ይታዎቃል፡፡ የክልሉ መንግስት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ዛሬ ማለዳ በአቫንቲ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት በደረሰው አደጋ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ከፍተኛ ሀዘን የተሰማቸው መሆኑን ገልፀዎል፡፡ አቶ ንጉሱ አያይዘውም በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ለሟች ቤተሰቦችና ለመላ ለሀገራችን ህዝቦች የክልሉ መንግስት መፅናናትን ይመኛል ብለዎል፡፡ በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን ብሎም የሟቾችን ቤተሰቦች በዘላቂነት ለማቋቋም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ የክልሉ መንግስት የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን ገልፀዎል፡፡