CURRENT

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ነገ ይጀምራል

By Admin

March 12, 2017

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ነገ ማካሄድ ይጀምራል።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ጽህፈት ቤት ባደረሰን መረጃ ለአራት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ፥ የበጀት አመቱ ስድስት ወራት የክልሉ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

የአስፈጻሚ አካላት የተቃለለ የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ፣ የክልሉ የዳኝነት አካላት አፈጻጸም እቅድና የዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት የክዋኔ ኦዲት አፈጻጸም ሪፖርቶችም ቀርበው ይገመገማሉ።

የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አቶ ይርሳው ታምሬ፥ ምክር ቤቱ በየዘርፉ የተፈጸሙ ተግባራትን የሚገመግም ቋሚ ኮሚቴ አቋቁሞ ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።

አፈጻጸሙ ቀርቦም እንደሚገመገምና የህዝብ ጥያቄን መሰረተ ያደረጉ ጉዳዮች ትኩረት እንደሚያገኙ ተገልጿል።

በጉባኤው ለልማት፣ መልካም አስተዳደርና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አጋዠ የሆኑ አዋጆችም ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።