የአማራ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ መደበኛ ጉባኤውን ከመጋቢት 4 2009 ጀምሮ በባህርዳር ከተማ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ይርሳው ታምሬ አንደገለጹት፥ ጉባኤው በክልሉ አስፈጻሚ አካላት የስድስት ወራት እቅድ ክንውንና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ይመክራል።
በተጨማሪም በጥልቅ ተሃድሶው ማግስት የመጡ ለውጦችን በመገምገም የተለያዩ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍና ሹመቶችንም እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
የምክር ቤቱ ጉባኤ ከመጋቢት 4 2009 ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ቀናት የሚካሄድ መሆኑን አፈጉባኤው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።