Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ በተደረገ ጥናት በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ እንዲቀጥል 82 በመቶ ድጋፍ አግኝቷል፡‑ ጠ/ሚ ኃይለማርያም

0 299

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ  ዛሬ መጋቢት 7፣2009 ያለፈውን ግማሽ አመት የመንግስታቸውን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡

በሪፖርታቸው  ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳቀረቡት አገሪቱ ተደቅኖባት የነበረውን አደጋ ለመቀልበስ ላለፉት አምስት ወራት ስራ ላይ የዋለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዓላማውን ማሳካቱን ተናግርዋል፡፡በቀጣይም ቢሆን  አዋጁን ደረጃ በደረጃ እያላሉ ለመሄድ የሚያችል አሰራር በመተግበር ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ስለመነሳት አለመነሳቱ በተደረገ ጥናት 82 በመቶ የሚሆነው የጥናቱ ተሳታፊዎች አዋጁ በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ እንዲቀጥል ምላሽ ሰጥተዋል ብለዋል፡፡

በመሆኑም  በጥናቱ በመመስረትና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርዱን የውሳኔ ሀሳብ መነሻ በማድረግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ  መቀጠል አለመቀጠሉ የሚወሰን መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም በሪፖርታቸው በኢህአዴግ ደረጃ የተጀመረው የጥልቅ ተሃድሶ ወደ ሁሉም የህብረተሰቡ ክፍል እንዲገባ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡በተሃድሶው በተለይም የህብረተሰቡን ፍትሃዊ የሀብት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በጥልቀት መታደሱ በሂደት እየሰፋ የታለመውን ለውጥ ለማምጣት ይሰራልም ብለዋል፡፡በተለይም ከተሃድሶው ጋር በተያያዘ ከሲቪክ ማህበራትና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ለመስራት የተጀመረው ጥረት መልካም መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩ እየሰፋ እንዲሄድ የተጀመረው የፖለተካ ፓርቲዎች ምክክርም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡በድፕሎማሲው ዘርፍ የአገሪቱን ጥቅም የሚያከብሩ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው ስራዎች መሰራታቸውንም አመልክተዋል፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት ከጎረቤትና ኢጋድ አባል አገራት ጋር  እንዲሁም ኢትዮጵያ በአባይ ተፋሰስ  አገራት ጋርም የመሪነት ሚና በመውሰድ ጥቅሞቿን ለማስከበር የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ ያለው ሰላም ወደ ቀድሞ ይዞታው እንዲመለስ ከአገራቱ ጋር እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ የኤርትራ መንግስትን ሸሽተው ለሚመጡ ስደተኞች የሚደረገው  ወንድማዊ መስተንግዶ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በአንፃሩ የሻዕቢያ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ እኩይ ተግባር ለመፈጸም መልምሎና አሰልጠኖ የሚልካቸው ኃይሎችን እያሰማራ መሆኑን ተናግረው ፣ህዝብ ከመንግስት ጎን በመቆም ሰርጎ ገቦችን ለመደምሰስ ለተጫወተው ሚና ምስጋና አቅርበዋል፡፡በመካከለኛው ምስራቅ ፣ከኢሲያ ሌሎች ተፅዕኖ ፈጣሪ የምዕራቡ አገራት ጋር በቅርበት ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂ ነድፎ  እየተሰራ መሆኑንም ተመልክቷል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy