የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሃድሶ ንቅናቄ የደረሰበት ሁኔታ እና የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን አፈፃፀም ሪፖርት መገምገም ጀመረ።
የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት በመግለጫው እንዳስታወቀው፤ ኮሚቴው ሪፖርቱን ከገመገመ በኋላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ጀምሯል።
ኮሚቴው ኢህአዴግ በይፋ የጀመረውን በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ ከአመራር አባላቱና ከአባሉ አልፎ ወደ ሲቪል ሠራተኛውና ህዝቡ እንዲወርድ የተቀመጠው አቅጣጫ የታሰበለትን ዓላማና ግብ በትክክል ማሳካት አለማሳካቱን በዝርዝር ይገመግማል።
በመግለጫው እንደተጠቀሰው፤ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር ወኪል የሆኑት ትምክህት፣ ጠባብነትና የኃይማኖት አክራሪነት እንዲሁም ሥልጣንን ለግል ጥቅም የማዋል አመለካከትና ተግባር የድርጅቱና አገራዊ የህዳሴ ጉዞ የሚፈታተኑ አደጋዎች መሆናቸው ታውቋል።
የኮሚቴው አባላት እነዚህ ተግባራት ህዝብን ጨምሮ በየደረጃው ትግል እንዲደረግባቸው የተቀመጠው አቅጣጫ የደረሰበት ሁኔታ በዝርዝር እንደሚገመግሙ ነው የተመለከተው።
ዴሞክራሲያዊ የመድበለ ፓርቲ ስርዓቱን ይበልጥ ከማጠናከር አኳያም በሕጋዊ መንገድ ከተደራጁ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር እየተደረገ ያለው ውይይትም እንደሚገመገም ያመለከተው መግለጫው፤ በቀጣይ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ጠቁሟል።
ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በየደረጃው ህዝቡ ሲያነሳቸው የነበሩ እና “ፈጣን ምላሽ ያሻቸዋል” ተብለው የተለዩ ጉዳዮች አፈፃፀም በዝርዝር ይገመግማል።
ኮሚቴው በግምግማው የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የሁለተኛው ዓመት አጋማሽ አፈፃፀም ሪፖርትንም በዝርዝር እንደሚገመግም ተመልክቷል።
በዚህም የማክሮ ኢኮኖሚ፣ የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ልማት ዘርፎች፣ የልማታዊ መልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ውይይት ተደርጎበት አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተገልጿል።
በተጨማሪም ኮሚቴው የሴቶችና የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በተመለከተም የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ እንቅስቃሴው አፈፃፀሞችን በዝርዝር በመፈተሽ ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ስብሰባ በነገው ዕለትም ቀጥሎ እንደሚውል የጽሕፈት ቤቱ መግለጫ ያመለክታል።
ጥልቅ ተሃድሶው በእውነት ከሆነ ጥሩ ነው ነገር ግን አሁንም ግን ጥልቀቱ እጠራጠረዋለሁ፡ በ4ቱ የአገሪቱ አቅጣጫ በጥልቀት መታደሱን በአንድ ክልል ያተኮረ ጥልቀት ይሰማኛል፡ እስቲ በእውነት እንያቸው በጥልቀት የታዩ ጥያቄዎች እኮ ፡ በአንድ ክልል በአገሪቱ የበላይነት አለው፡ ወይስ የለውም ፡ ፌደራል መንግስት ለአንድ ክልል ፋብሪካዎች እያጎረፈ ነው፡ አሁንም ስልጣን ለአንድ ክልል ተወላጆችን እየሰጠ ነው …እና ሌሎች ለአንድ ክልል ብቻ ያተኮሩ ሃሳቦች በጥልቀት የታዩበት ሁኖ ያለፈ ይመስለኛል፡ እንደ ኔ የሀ ነገር ትክክል ነው ብየ ኣላምንም፡ ለምሳሌ የጎረፎላቸው ፋብሪካዎች እያቃጠሉ ፌብሪካዎች ወደ አንድ ክልል እየጎረፉ ነው ማለት ምንድ ነው፡ 200 ከዛ በላይ የመንግስት ፋብሪካዎች ያለው ክልል ለ20 የግል ፋብሪካዎች ያሉት ክልል የበላይነት አለው ማለትስ ምንድነው፡ የአንድ ክልል ተወላጅ አንድ ሰው ወደ ስልጣን ሲወጣ ሺ አይኖች የሚያይበት ነገርግን 50 ሰው የሌለው ክልል ተወላጅ ወደ ስልጣን ሲመጡ አይኖች የሚጨፈንበት ምክንያት ምንድ ነው፡ በዚ ጉደይ ቡዙ ግንዛቤ ከሌለው በሚጣ ችግር አልነበረውም ነገር ግን አገር ከሚመሩት ሙሁራን እንደዚሁ መምጣቱን እና እንደ አቋም ይዞ መራመዱ ግን፡ለኔ ሚዛናውነቱ የጎደለው ግምገማ እንደነበረ ያየሁበት ግምገማ ነበር እላለሁ፡ በዚህም የራስህን በጥልቀት ከማየት በሌላው ጫፍ ያተኮረ ግምገማ ብለው ቅር አይለኝም ፡ ስለዚህ እንደመንግስት ትኩረት ያስፈልገዋል የሚለው አስተያየት አለኝ
ጥልቅ ተሃድሶው በእውነት ከሆነ ጥሩ ነው ነገር ግን አሁንም ግን ጥልቀቱ እጠራጠረዋለሁ፡ በ4ቱ የአገሪቱ አቅጣጫ በጥልቀት መታደሱን በአንድ ክልል ያተኮረ ጥልቀት ይሰማኛል፡ እስቲ በእውነት እንያቸው በጥልቀት የታዩ ጥያቄዎች እኮ ፡ በአንድ ክልል በአገሪቱ የበላይነት አለው፡ ወይስ የለውም ፡ ፌደራል መንግስት ለአንድ ክልል ፋብሪካዎች እያጎረፈ ነው፡ አሁንም ስልጣን ለአንድ ክልል ተወላጆችን እየሰጠ ነው …እና ሌሎች ለአንድ ክልል ብቻ ያተኮሩ ሃሳቦች በጥልቀት የታዩበት ሁኖ ያለፈ ይመስለኛል፡ እንደ ኔ የሀ ነገር ትክክል ነው ብየ ኣላምንም፡ ለምሳሌ የጎረፎላቸው ፋብሪካዎች እያቃጠሉ ፌብሪካዎች ወደ አንድ ክልል እየጎረፉ ነው ማለት ምንድ ነው፡ 200 ከዛ በላይ የመንግስት ፋብሪካዎች ያለው ክልል ለ20 የግል ፋብሪካዎች ያሉት ክልል የበላይነት አለው ማለትስ ምንድነው፡ የአንድ ክልል ተወላጅ አንድ ሰው ወደ ስልጣን ሲወጣ ሺ አይኖች የሚያይበት ነገርግን 50 ሰው የሌለው ክልል ተወላጅ ወደ ስልጣን ሲመጡ አይኖች የሚጨፈንበት ምክንያት ምንድ ነው፡ በዚ ጉደይ ቡዙ ግንዛቤ ከሌለው በሚጣ ችግር አልነበረውም ነገር ግን አገር ከሚመሩት ሙሁራን እንደዚሁ መምጣቱን እና እንደ አቋም ይዞ መራመዱ ግን፡ለኔ ሚዛናውነቱ የጎደለው ግምገማ እንደነበረ ያየሁበት ግምገማ ነበር እላለሁ፡ በዚህም የራስህን በጥልቀት ከማየት በሌላው ጫፍ ያተኮረ ግምገማ ብለው ቅር አይለኝም ፡ ስለዚህ እንደመንግስት ትኩረት ያስፈልገዋል የሚለው አስተያየት አለኝ፡፡