Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ

0 1,647

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

  •  የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ዛሬ የጀመረው ስብሰባ የጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄው የደረሰበት ሁኔታ እና የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ሁለተኛ ዓመት የግማሽ አመት አፈፃፀም ሪፖርትን በዝርዝር በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል።

ግምገማው ጥልቀትና ስፋት ይኖረው ዘንድ በቂ ዝግጅት መደረጉም ተገልጿል።

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ኢህአዴግ በይፋ የጀመረው እንደገና በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ ከአመራሩና ከአባሉ አልፎ ወደ ሲቪል ሰርቫንቱና ህዝቡ እንዲወርድ የተቀመጠው አቅጣጫ የታሰበለትን ዓላማና ግብ በትክክል ማሳካት አለማሳካቱን በዝርዝር መገምገም ጀምሯል።

የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር ወኪል የሆኑት ትምክህት፣ ጠባብነትና የሃይማኖት አክራሪነት እንዲሁም ስልጣንን ለግል ጥቅም የማዋል አመለካከትና ተግባር ድርጅቱንና ሀገራዊ የህዳሴ ጉዞውን የሚፈታተኑ አደጋዎች በመሆናቸው ህዝቡን ጨምሮ በየደረጃው ትግል እንዲደረግባቸው የተቀመጠው አቅጣጫ የደረሰበት ደረጃም በዝርዝር ይገመገማል፡፡

ዴሞክራሲያዊ የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱን ይበልጥ ከማጠናከር አንፃርም በሕጋዊ መንገድ ከተደራጁ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር እየተደረገ ያለውን ውይይት በመገምገም በቀጣይ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይም ኮሚቴው አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ይሆናል።

በየደረጃው ህዝቡ ሲያነሳቸው የነበሩና ፈጣን ምላሽ ያሻቸዋል ተብለው የተለዩ ጉዳዮችን አፈፃፀም እንዲሁም የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በተመለከተ በተለይም የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ እንቅስቃሴው የደረሰበትን ደረጃ በዝርዝር በመገምገም አቅጣጫም እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በግምግማው የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ሁለተኛ ዓመት የግማሽ አመት አፈፃፀም ሪፖርትንም በዝርዝር እየገመገመ ይገኛል።

በዚህም የማክሮ ኢኮኖሚ፣ የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ልማት ዘርፎች፣ የልማትና መልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲሁም የሴቶችና የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት አፈፃፀሞችን በዝርዝር በመፈተሽ ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሏል።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በነገው ዕለትም ቀጥሎ እንደሚያካሂድ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ገልጿል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy