Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ግንባታ ለታዳጊ አገራት ትምህርት የሚሆን ነው -ፒተር ቶምሰን

0 928

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት ግንባታ ስራ ታዳጊ የአፍሪካ አገራት ትምህርት የሚወስዱበት መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ፒተር ቶምሰን ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱና ሌሎች የልዑካን ቡዱን አባላት ዛሬ በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ዞን የጨርቃ ጨርቅና ጫማ ፋብሪካዎችን ጉብኝተዋል።

ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው ወቅት ለጋዚጠኞች እንደገለጹት ”ኢትዮጵያ በዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት ግንባታ የምታደርገውን ጥረት ስሰማ ነበር፣ ዛሬ ግን እዚሁ ተገኝቼ የጨርቃጨርቅና የጫማ ፋብሪካዎችን መመልከት ችያለሁኝ።”

ይህ ደግሞ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማትን እውን ከማድረግ ባለፈ በአህጉሩ የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች መሆንዋን  ያሳያል ብለዋል።

ታዳጊ የአፍሪካ አገራት ከኢትዮጵያ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት ግንባታ ስራ ትምህርት ሊወስዱ እንደሚገባም ነው የገለጹት።

በአገራቸው የጨርቃጨርቅና ጫማ ፋብሪካዎችን የስራ ሁኔታ እንደሚያውቁ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ “የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዞን ግንባታ የሚደነቅ ነው” ብለዋል።

ሀገሪቱ ለዜጎቿ የስራ ዕድል በመፍጠርና  ፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ልማት ለመገንባት የምታደርገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ፋብሪካዎች የሚጠቀሙት ሃይል ከታዳሽ ሃይል መሆኑ አገሪቱ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የያዘችውን እቅድ ትክክለኛነት ያረጋግጣልም ብለዋል ፕሬዘዳንቱ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዝዳንት ፒተር ቶምሰን በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ሲሆኑ በነገው ውሏቸው ከአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽንና ከህብረቱ  መሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy