Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒን የሚወስዱ ሴቶች ለ30 ዓመታት በካንሰር የመያዝ እድል የላቸውም- ጥናት

0 2,786

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ለ44 ዓመታት በተደረገ ጥናት የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒን የሚጠቀሙ ሴቶች ለ30 ዓመታት ያህል በካንሰር ያለመያዝ እድል እንዳላቸው አንድ ጠናት ጠቁሟል።በጥናቱ መሰረት የወሊድ መቆጣጠሪያ የወሰዱ ሴቶች ካልወሰዱት በተሻለ ለአንጀት፣ ለማህፀን እና ለዘር ፍሬ አካል ካንሰር የመያዝ እድላቸው ዝቅተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ጥናቱ በስኮትላንድ በሚገኘው ጥንታዊው አበርዴን ዩኒቨርሲቲ የተመራ ሲሆን ለ44 ዓመታት ረጅም የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒን የወሰዱ ሴቶችን መረጃ (ዳታ) በማጥናት ነው ውጤቱን ያገኘሁት ብሏል፡፡

የወሊድ መቆጣጠሪያ በወሰዱት ሴቶች ላይ ሁሉም የካንሰር ዓይነቶች ሊያደርሱ የሚችሉትን ጉዳት ተመልክቷል ጥናቱ፡፡የጥናቱ ውጤት መውለድ በሚችሉባቸው ዓመታት መቆጣጠሪያ ክኒን የወሰዱ ሴቶች በህይወታቸው ላይ አዲስ የካንሰር ህመም እንደማያጋጥማቸው አመላክቷል፡፡

መነሻውን በ1968 ያደረገው ይህ ጥናት በአፍ የሚወሰዱ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ ከዚሁ ጋር የተያያዙ የጤና ለውጦችን በዝርዝር ተመልክቷል ነው የተባለው፡፡ለ44 ዓመታት ያህል በ46 ሺህ ሴቶች ላይ ክትትል በማድረግ ነው የጥናቱ ግኝት ይፋ የሆነው፡፡

ጥናቱ ሲካሄድ የተሳተፉት በአቨሬደን ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ተመራማሪው ዶክተር ሊሳ ኢቨርሰን እንዳሉት፥ በ44 ዓመታት ውስጥ በተተነተነው ጥልቅ መረጃ የተገኘው ውጤት የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒን የሚጠቀሙ ሴቶች የማህፀን፣ የአንጀት እና የዘር ፍሬ አካል ካንሰር እንደማያጠቃቸው ነው የሚያሳየው፡፡

በወጣትነት ዘመናቸው የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚወስዱ ሴቶች በቀሪ የእርጅና ዘመናቸው ምንም ዓይነት የካንሰር ህመም እንደማያገኛቸው የሚያመላክት ውጤት መገኘቱን ዶክተር ኢቨርሰን ተናግረዋል።

ምንጭ፡- www.dailyrecord.co.uk/

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy